ትራምፕ በመወለድ የሚገኝ ዜግነትን ለመገደብ ሁለት አዲስ ትዕዛዞች አስተላለፉ

የፎቶው ባለመብት, Bloomberg via Getty Images
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሁለት አዲስ ትዕዛዞችን በማስተላለፍ በመወለድ የሚገኝ ዜግነትን ለመገደብ የሚያደርጉትን ሙከራ ቀጥለዋል።
የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ትራምፕ በመወለድ የሚገኝ ዜግነትን ለማስቀረት ያደረጉትን ሙከራ ውድቅ ቢያደርግም ፕሬዝዳንቱ ትናንት ሐሙስ ያስተላለፉት ትዕዛዝ ከዚህ ይቃረናል።
ትራምፕ ትናንት ከፈረሙበት ትዕዛዝ አንዱ የአሜሪካ ዜጋ ያልሆኑ ሰዎች ልጆቻቸው ዜግነት እንዲያገኙ የሚያደርገውን አሠራር ትርጓሜውን የሚያሰፋ ነው።
ሁለተኛው ትዕዛዝ ነፍሰ ጡር ሴቶች ወደ አሜሪካ ለጉብኝት ሄደው እዚያው በመውለድ ልጆቻቸው ዜግነት የሚያገኙበትን አሠራር ይመለከታል።
ትራምፕ "ከዓመታት በፊት መተግበር የነበረበት ቢሆንም አሁን እያደረግነው ነው" ብለዋል።
ሰነድ አልባ ስደተኞች በአሜሪካ የሚወልዷቸው ልጆች የአሜሪካ ዜግነት እንዳያገኙ ለማገድ ትራምፕ ያደረጉትን ጥረት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውድቅ ማድረጉን ተችተዋል።
ይህ ሕግ በአሜሪካ 150 ዓመታት ያስቆጠረ ነው።
"ክፉ የሆኑ የውጭ አካላት የአሜሪካን ደግነት በመበዝበዝ ዜግነት ለማግኘት መሞከራቸው ለማስቆም አስተዳደራችን ይሠራል" ብለዋል።
ትራምፕ ያስተላለፏቸው ትዕዛዞች አሜሪካዊ ካልሆኑ ወላጆች የሚወለዱ ልጆች ዜግነት የሚያገኙበትን አሠራር ይገድባል።
ከወላጆች አንደኛቸው የውጭ አገር የሽብር ቡድን አባል ከሆኑ፣ የውጭ መንግሥት መሥሪያ ቤት ሠራተኛ ከሆኑ፣ በማጭበርበር ዜግነት ለማግኘት ከሞከሩ ወይም በአሜሪካ የሚኖሩት ያለ ፌደራል መንግሥት የዜግነት ዕውቅና ሳይሰጣቸው ከሆነ ልጆቻቸው የአሜሪካ ዜግነት አያገኙም።
በአሜሪካ የሚወለዱ ሰዎች ዜግነት የማግኘት መብት አላቸው። የትራምፕ አስተዳደር ይሄንን ለመቀልበስ በተደጋጋሚ ጥረቶች አድርጓል።
በአሜሪካ መወለድ የሚያስገኘውን የዜግነት መብት ሩሲያ እና ቻይና እየበዘበዙት ነው ሲሉ ትራምፕ ከስሰዋል።
ነፍሰ ጡር ሴቶች ወደ አሜሪካ ለቱሪዝም በመጓዛቸው በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ልጆች በአሜሪካ መወለዳቸውን ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።
ገለልተኛ የጥናት ተቋም የሆነው 'ዘ ማይግሬሽን ፖሊሲ ኢንስቲትዩት' እንዳለው በየዓመቱ አሜሪካ ለቱሪዝም ሄደው ከሚወልዱ ነፍሰ ጡሮች የሚወለዱ ልጆች ከ22,000 እስከ 26,000 ይደርሳሉ።
የመንግሥት አሐዝ እንደሚያሳየው በአውሮፓውያኑ 2024 የውጭ አገራት ዜጎች ከሆኑ እናቶች 9,600 ልጆች ተወልደዋል።
የአገር ውስጥ ደኅንነት አማካሪ እና የዋይት ሀውስ ምክትል ኃላፊ "ሰዎች ቱሪስት ነን ብለው በማስለመሰል ይመጣሉ" በማለት ትራምፕን እንደሚደግፉ ተናግረዋል።
"እውነተኛ እዚህ የሚመጡበት ምክንያት ግን ልጅ ለመውለድ እና ዜግነት እንዲያገኙ ለማድረግ ነው። ከአገራችን ውጡና ልጆች ውለዱ" ሲሉም አክለዋል።
እነዚህ ልጆች "የአሜሪካውያን መብት የሆኑ" መምረጥ እና ደኅንነትን ጨምሮ ሌሎችም ጥቅማ ጥቅሞች እንደሚያገኙ ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንቱ በስደተኞች እና ብሔራዊ ድንጋጌ መሠረት ወደ አሜሪካ ለቱሪዝም የሄዱ ነፍሰ ጡሮች ልጆቻቸው የአሜሪካ ዜጋ የሚሆኑበትን መብት መቀልበስ ይችላሉ ብለዋል።
ወደ አሜሪካ የሚገቡበት አሠራር ላይ ገደብ ሊጥሉም ይችላሉ በሚል ተናግረዋል።
የአሜሪካ ሕገ መንግሥት 14ኛ አንቀጽ አሜሪካ ውስጥ መወለድ ዜግነት እንደሚያስገኝ ይደነግጋል።
ጉዳዩ ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከተወሰነ በኋላ ፍርድ ቤቱ የትራምፕ ውሳኔ ሕጉን እንደማይቀለብስ አስታውቋል።
ትራምፕ አሜሪካ የሚኖሩ፣ የሚሠሩ እና ዜግነት የሚያገኙ ሰዎችን ለመገደብ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ላይ ጫና ያሳደረ ውሳኔም ነው።
"ፍርድ ቤቱ መጥፎ ውሳኔ ነው ያሳለፈው፤ ፍትሐዊ አይደለም" ሲሉ ትራምፕ ተችተዋል።
በመወለድ የሚገኝ ዜግነት "አገራችንን እየጎዳ ነው" ያሉት ፕሬዝዳንቱ ይሄንን አሠራር እንደሚያስቆሙም ገልጸዋል።
በካሊፎርንያ፣ ዳቪስ ስኩል ኦፍ ሎው የሚሠሩት ፕ/ር ጋብርዬል ቺን ለቢቢሲ እንደገለጹት የትራምፕ ትዕዛዞች "ጠንካራ ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄዎች" ያስነሳሉ።
ሰዎች ልጅ ለመውለድ በሚል ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ማድረግ እንደማይቻልም ይናገራሉ።
"አንድ ልጅ አሜሪካ ከተወለደ በኋላ ፕሬዝዳንቱ ዜግነት መከልከል የሚችሉበት ሥልጣን አለ ብዬ አላስብም" ይላሉ።
የትራምፕ ውሳኔ በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ መቀልበሱንም ያክላሉ።















