ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ የስደተኞችን አደገኛ ጉዞ ለማሳየት ካናሪ ደሴትን ጎበኙ

የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ፖፕ ሊዮ 14ተኛ

የፎቶው ባለመብት, EPA/Shutterstock

የምስሉ መግለጫ, ፖፕ ሊዮ ካናሪ ደሴት ለመድረስ ሲሉ ሕይወታቸውን ላጡ ስደተኞች ማስታወሻ የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል
ታትሟል
የንባብ ጊዜ: 2 ደቂቃ

የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፖፕ ሊዮ 14ተኛ አውሮፓ ለመድረስ አትላንቲክ ውቅያኖስን የሚያቋርጡ ስደተኞችን ረዥም እና አደገኛ ጉዞ በመስማት በካናሪ ደሴት የሁለት ቀናት ጉብኝታቸውን ሐሙስ ጀመሩ።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በስፔን ግራን ካናሪያ ደሴት ለተሰባሰቡት "እናንተ ቁጥሮች አሊያም በራሪዎች አይደላችሁም፤ ሰዎች ናችሁ" ያሉ ሲሆን፤ ከክብራችሁ በታች "አንገቴን እደፋለሁ" ሲሉ አክለዋል።

እውቅና መስጠቱ እና አጋርነቱ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሱ የደሴት ጉዞ ዋና መልዕክት ነው። በአውሮፓ እና በሌሎች ስደተኞችን እንደ ቀውስ እና ወራሪ አድርጎ ለማየቱ ጉዞው ግልፅ መልስ ሆኖ ታይቷል።

ከመንግሥታቱ ድርጅት ከፍተኛ የስደተኞች ኮሚሽን የወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በዚህ ዓመት ወደ ስፔን በባሕር የሚገቡ ስደተኞች ቁጥር አሽቆልቁሏል።

ለዚህም ከዋና ምክንያቶች ውስጥ በአውሮፓ ህብረት የገንዘብ ድጋፍ ከምዕራብ አፍሪካ የባሕር ዳርቻዎች የሚነሱ ጀልባዎችን ማስቆም ጠንከር ማለቱ አንዱ ነው።

ይሁን እንጂ በርካታ ሰዎች ለመሻገር አሁንም እየሞከሩ እና ሕይወታቸውን እያጡ ነው።

በአብዛኛው ስደተኞች ጥቅም ላይ በሚውለው የአርጉንጉን ወደብ ላይ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ከሁሉም በላይ አማራጭ "ሕጋዊ እና ደኅንነቱ የተጠበቀ መተላለፊያ" እንደሚያስፈልግ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

"አውሮፓ ህሊና እንዲኖረው" ጥሪ ያቀረቡት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ባሕሮቹ ስም ያልተፃፈባቸው የቀብር ስፍራ ወይንም በርካቶች ሕይወትን ፍለጋ ህይወታቸውን አደጋ ላይ የሚጥሉበት ስፍራ መሆናቸውን "መላመድ" የለባቸውም ብለዋል።

Skip podcast promotion and continue reading
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናል

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት

ይህንን በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

End of podcast promotion

ይህም አንድ ጀልባ ሙሉ ስደተኞች የት እንደገቡ እንኳ ሳይታወቅ መጥፋታቸውን ያካትታል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ሕይወታቸውን ላጡ ማስታወሻ ይሆን ዘንድ በማዕበሎቹ የአበባ ጉንጉን ወርውረው ለፀሎች አንገታቸውን ዝቅ አድርገዋል።

ባካሪ ጃጁ ከእድለኞቹ መካከል እንደሆነ ይናገራል።

የተሻለ ሕይወትን በመፈለግ ከጋምቢያ በእንጨት ጀልባ ላይ ሲወጣ ገና 19 ዓመቱ ነበር። ለሰባት አስፈሪ ቀናት ባሕር ላይ ሲያሳልፍ የምግብ እና ውሃ አቅርቦት እያለቀ ነበር።

"ሞትኩም ተረፍኩም ለመሄድ ወሰንኩ። ምክንያቱም ቤተሰቦቼ ጥሩ ሁኔታ ውስጥ እንዲሁኑ ስለምፈልግ" ይላል ባካሪ ባለቤቱን እና ልጁን ጥሎ ለመሰሰድ እና በአደገኛ መንገድን ለመጓዝ ለምን እንደመረጠ ሲያብራራ።

160 ከሚሆኑ በጀልባው ውስጥ ከታጨቁ ሰዎች መካከል ሴቶች እና ሕፃናትም ነበሩ። ኤል ሂሮ በተባለቸው የስፔን ደሴት አቅራቢያ ነዳጅ ጨርሰው እያለ ተገኝተው በመጨረሻም በሕይወት ድነዋል።

ባካሪ በሕጋዊነት መቆየት በሚያስችለው ፕሮጄክት እስኪታቀፍ ድረስ ሦስት "በጣም ብርዳማ፤ በጣም አስቸጋሪ" ወራትን በስደተኞች ካምፕ ለመቆየት ተገድዶ ነበር።

የዚህ ፕሮጀክት ጀርባ አባ ፔፔ የተባሉ ቄስ ናቸው።

የአባ ፔፔ ቡድን የስፔን መንግሥት ሰነድ አልባ ስደተኞችን ሕጋዊ ለማድረግ ያቀረበው የጊዜ ገደብ ሳያልቅ ሁሉንም ለመርዳት እየተሯሯጠ ነው።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ተኛ በስደተኞች ዙሪያ ያለውን አቋም ለመቀየር እየሞከሩ ባለበት በዚህ ወቅት የአውሮፓ ህብረት ድንበሮቹን የበለጠ ጠበቅ ለማድረግ የደረሰው ስምምነት በዚህ ሳምንት ጀምሯል።

ይህ ሀሳብ በባሕር የሚደርሱ ስደተኞችን በቁጥጥር ስር ለማዋል እና ወደ አገራቸው ለማባረር ቀላል ማድረግ ነው።

እንደ ባካሪ ጃጁ ላሉ ሁሉንም መስዋዕት ለማድረግ ለተዘጋጁት ይህ እርምጃ መጠነኛ እግድ ሲሆን፤ ሰብዓዊ መብት ቡድኖች ለጥገኛ ጠያቂዎች እና ጉዳያቸው እንዲሰማ ለሚየሳልፉት ውጣ ውረድ ደግሞ አዲስ ፍርሃትን ፈጥሯል።