ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ፊፋ ከእያንዳንዱ የዓለም ዋንጫ በቢሊዮን ዶላሮች ገቢ የሚያገኘው እንዴት ነው?
በዓለም ዋንጫ ምርጡ ግብ አግቢ የወርቅ ጫማ፣ ምርጡ ግብ ጠባቂ ደግሞ የወርቅ ጓንት ይሸለማሉ። በዚህ ዓመትም የዓለም ዋንጫ አዘጋጅ የሆነው ፊፋ ከቲኬት ሽያጭ ቢሊዮን ዶላሮችን በመሰብሰብ ወርቃማ ዕድል አግኝቷል።
የዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ትኬት ውድ ከመሆኑ የተነሳ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ራሳቸው ለመግዛት እንደማይችሉ ተናግረዋል።
ይህም ፊፋ የእግር ኳሱ ቀንደኛ ደጋፊዎች ከስታዲየሞች እንዲርቁ ያደርጋቸዋል የሚል ስጋት ፈጥሯል።
በ2022 በኳታር የተካሄደው የዓለም ዋንጫ ደረጃ አንድ ቲኬት ዋጋ 220 የአሜሪካ ዶላር የነበረ ሲሆን፣ ለአንዳንድ ጨዋታዎች እስከ 11 ዶላር ተሽጦ ነበር።
የፍጻሜ ጨዋታ ደረጃ አንድ ትኬት 1600 ዶላር ተሽጧል።
በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ላይ ግን ለመጀመሪያ ጊዜ የቲኬት መሸጫ በጨዋታዎች መካከል እንዲለዋወጥ እንዲሁም ለተመሳሳይ ጨዋታ ትኬቶች በሚሸጡበት ጊዜ የዋጋ ለውጥ ተደርጓል።
የ2026 የዓለም ዋንጫ የምድብ አንድ ቲኬቶች በ2025 ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሽያጭ ሲቀርቡ ወደ 600 የአሜሪካ ዶላር አካባቢ ነበሩ። አሁን ግን በአጠቃላይ ከ1,000 የአሜሪካ ዶላር በላይ እና አንዳንዴም ከዚያ በላይ ይሸጣሉ።
የምድብ 1 ትኬቶች በሜክሲኮ ሲቲ ለሚካሄደው የመክፈቻ ጨዋታ ከ2,500 የአሜሪካ ዶላር በላይ ተሽጠዋል። የምድብ 3 ትኬቶች ደግሞ ዝቅተኛው ደረጃ ያላቸው ሲሆን ከ1,000 የአሜሪካ ዶላር በላይ ይጠይቃሉ።
ለመጨረሻው ውድድር የምድብ 1 ትኬቶች መጀመሪያ ላይ ከ6,000 የአሜሪካ ዶላር በላይ ዋጋ የተተመነላቸው ሲሆን፣ በግንቦት ወር መጀመሪያ ላይ ደግሞ ከ32,000 የአሜሪካ ዶላር በላይ ደርሰዋል።
የስፖርት ምጣኔ ሀብት ፀሐፊ የሆኑት የፋይናንስ ፕሮፌሰር ሪቻደድ ሺሃን የቲኬት ገቢ መጨመር ፊፋ በዚህ የዓለም ዋንጫ ከ15 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ በላይ እንደሚያገኝ ስሌቶችን ሠርቻለሁ ይላሉ።
ይህም ለዓለም እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ክብረወሰን እንደሚሆን እና በ2022 ከተጠቀሰው 11 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ በእጅጉ የላቀ ነው።
ፊፋ ያገኘውን በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ገቢ ምን ላይ ለማዋል ዕቅድ እንዳለው ግልጽ አይደለም። ምክንያቱም አዎንታዊ ማኅበራዊ ለውጥን የመደገፍ ዓላማው በሙስና እና በግልጽነት እጦት ምክንያት የጠለሸ ነው።
ፊፋ የሚሠራው እንዴት ነው?
የቲኬቶችን ዋጋ ከፊፋ የፋይናንስ እና አጠቃላይ ግቦች አንፃር ማስቀመጥ አስፈላጊ ነው።
ፊፋ በስዊትዘርላንድ እንደ በጎ አድራጎት ድርጅት የተመዘገበ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሲሆን፣ ሥልጣኑ እንደ የዓለም ዋንጫ ያሉ ውድድሮችን ማዘጋጀት ብቻ ሳይሆን እግር ኳስን ማስተዋወቅ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የስፖርቱን ተደራሽነት ማስፋት ነው።
ማኅበሩ በአራት ዓመት የበጀት ዑደት ውስጥ የሚሠራ ሲሆን አብዛኛውን ገቢ የሚያገኘው ባለፈው የውድድር ዓመት ከተካሄደው የዓለም ዋንጫ ነው።
ታሪካዊ ንጽጽሮች የጉዳዩን አውድ ለመረዳት ያግዛሉ። ብዙዎች ትልቅ ስኬት እንደሆነ አድርገው የሚቆጥሩት የ1994ቱ የአሜሪካ የዓለም ዋንጫ 700 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የተጣራ ገቢ፣ ወይም ትርፍ በማስገኘት በአብዛኛው ከሚጠበቀው በላይ በሆነ የቲኬት ሽያጭ እና ስፖንሰርሺፕ ምክንያት 550 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ አስገኝቷል።
ትላልቅ ስታዲየሞች እና ከፍተኛ የተመልካቾች ቁጥር በአሜሪካ ውስጥ የዋና ሊግ ውድድርን ጨምሮ የፊፋ የልማት ግቦችን ለማሳደግም ረድቷል።
በ2022 የፊፋ የፋይናንስ አቅም በሚያስደንቅ ሁኔታ አድጓል። የዚያን ዓመት የዓለም ዋንጫን ጨምሮ ለነበረው ውድድር ገቢ 6.44 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንደሚደርስ ቢገመትም 7.57 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ደርሷል። አብዛኛው ዕድገት ከብዙኃን መገናኛዎች እና ከማስታወቂያ ነው።
በኳታር ውስጥ አነስተኛ ሜዳዎች በመኖራቸው ምክንያት የተመደበው የቲኬት ገቢ መጠነኛ ቢመስልም፣ ትክክለኛው የቲኬት ገቢ ከሚጠበቀው በላይ ነበር። ምናልባትም በፊፋ መደበኛ የገቢ ትንበያ ምክንያት ሊሆን ይችላል።
ወጪው ከበጀቱ ጋር በቅርበት የተጣጣመ ሲሆን፣ በ2019-2022 ዓመታት ውስጥ ለልማት ፕሮግራሞች 2.8 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ተመድቧል። ይህ ወጪ ቢኖርም የ2022ቱ ውድድር ስኬታማ በመሆኑ የመጠባበቂያ ገንዘቡ ከ2.81 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወደ 3.89 ቢሊዮን አድጓል።
የ2026ቱን የዓለም ዋንጫ በተመለከተ፣ ፊፋ ከ2019 እስከ 2022 ጋር ሲነጻጸር ገቢው በ4.36 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንደሚጨምር በጀቱን አስልቶ ነበር።
ይህም በአብዛኛው በቲኬት ሽያጭ ላይ በ2.59 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ጭማሪ እና የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት መብቶች እና በ890 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ጭማሪ በማሳየቱ ምክንያት 11 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንደሚደርስ አስታውቋል።
የፊፋ ወጪዎች በ4.57 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንደሚጨምሩ ይጠበቃል። ይህም ማለት ወደ 100 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚጠጋ ትርፍ እንደሚኖር ይጠቁማል። ይህም ከቀድሞው ውድድር ተመሳሳይ ትንሽ ጭማሪ ነበረው። የተሻሻለው የ2024 የፊፋ በጀት የ2023-2026 ወቅት የሚጠበቀውን ገቢ ወደ 13 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር አሳድጓል።
የፊፋ ተጽዕኖ በቲኬት ፍላጎት ላይ
የፊፋ ታሪክ መደበኛ የገቢ ትንበያዎች፣ ጥብቅ የወጪ ቁጥጥር እና በቲኬት ሽያጭ እና ፈቃድ አሰጣጥ ላይ ወጥ የሆነ ቁጥጥር፣ ከተጠበቀው በላይ ገቢ የሚያስገኙ ትኬቶች እና በመጨረሻ ሰዓት ቦታ የሚይዙ ላይ "ድንገቴ ውሳኔዎችን" ማሳለፍ የተለመደ ነው።
ይሁን እንጂ የቲኬት ሽያጭ ዋናው የገቢ ምንጭ እና ዋነኛው የውዝግብ ምንጭ ሆኖ ቀጥሏል። ውድድሩን ወደ 2026 ማስፋት ማለት ብዙ ቡድኖች፣ ተጨማሪ ግጥሚያዎች፣ ተጨማሪ አድናቂዎች እና ከፍተኛ የቲኬት ፍላጎት ማለት ነው።
ከ1994 ዓ.ም ጀምሮ ከማንኛውም የዓለም ዋንጫ በላይ የሆኑ ስታዲየሞች ቢኖሩም፣ ፍላጎቱ ከአቅርቦቱ እጅግ የላቀ ነው። በዕጣ ውስጥ ለመሳተፍ ከ500 ሚሊዮን በላይ ማመልከቻዎች የነበሩ ቢሆንም 7.1 ሚሊዮን መቀመጫዎች ብቻ ይገኛሉ።
ይህ አለመመጣጠን ለፊፋ ከፍተኛ የዋጋ አተማመን አቅም ሰጥቷል። ትችቶችን ለማቃለል ፊፋ በብሔራዊ ማኅበራት በኩል የተመደበ 60 ዶላር "የደጋፊዎች የመግቢያ ትኬቶች" አስተዋውቋል።
ሆኖም እነዚህ ትኬቶች የሚወክሉት ከአጠቃላዩ ጥቂቱን ብቻ ነው። በአንድ ጨዋታ ከ600 ያነሱ እና በዋጋዎቹ ላይ ያለውን ቁጣ ለማብረድ ብዙም የማያግዙ ናቸው።
አብዛኞቹ ቲኬቶች በተለዋዋጭ ዋጋ አሰጣጥ ደረጃዎች የተሸጡ ሲሆን፣ በደረጃዎቹ ውስጥ ከፍተኛ ጭማሪዎች ሲኖሩ፣ አብዛኞቹ ሽያጮች ደግሞ በኋለኞቹ እና በጣም ውድ በሆኑ ደረጃዎች ውስጥ ይከሰታሉ።
የስታዲየሞች አቀማመጥ የሚያሳዩ መዘርዝሮች አብዛኞቹ ቲኬቶች ከፍተኛ የዋጋ ምድብ ውስጥ እንደሚገኙ ያመለክታሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ ፊፋ ራሱ ከሚቆጣጠረው የድጋሚ ሽያጭ ገቢ ያገኛል።
እነዚህ ሦስት ምክንያቶች የቲኬት ገቢን የፊፋ በጀትን በእጅጉ ሊያሳድጉት ይችላሉ። በዚህ ተለዋዋጭነት ላይ በመመሥረት የቲኬት እና የመስተንግዶ ገቢ ቢያንስ 7.44 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንደሚሆን ይገመታል። ይህም ከፊፋ በጀት ከእጥፍ በላይ ነው። ነገር ግን ከስታዲየሙ አቅም በተለያዩ ደረጃዎች የዋጋ አተማመን የመቀመጫ ምደባ እና ቀጣይ የሽያጭ እንቅስቃሴ ጋር የሚጣጣም ነው።
በ2022 ከቲኬት ሽያጭ እና ከመስተንግዶ አገልግሎቶች የተገኘው ገቢ በአማካይ 14.5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ነበር። የዘንድሮው ግን የ3.1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በጀት በአንድ ግጥሚያ አማካይ የቲኬት ገቢ ወደ 30 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር አካባቢ እንደሚሆን ያሳያል።
ነገር ግን ትላልቅ ስታዲየሞች እና ከፍተኛ የቲኬት ዋጋዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ ይህ አሃዝ ከቲኬት ሽያጭ የሚገኘውን ትክክለኛ ገቢ በእጅጉ ዝቅ አድርጎ የሚመለከት ይመስላል።
የቲኬት ሽያጭ እና የመስተንግዶ አገልግሎቶች የመጨረሻ ዋጋ ወደ 9 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ቢጠጋ ምንም አያስደንቅም። የፊፋ አጠቃላይ የገቢ ትንበያ ከ14 ቢሊዮን እስከ 19 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር መካከል ነው።
ገንዘቡ የት ይሄዳል?
የእግር ኳስ ደጋፊዎች የቲኬት ገዢዎችም ሆኑ በሚዲያ የሚመለከቱ ለፊፋ ገቢ ያስገኛሉ።
በምላሹ ደግሞ የፊፋ ዓላማዎች እነዚያን ገንዘቦች ታላቅ የዓለም ዋንጫ ለማዘጋጀት እንዲሁም እግር ኳስን ለማስተዋወቅ እና ተደራሽ ለማድረግ መጠቀም ይኖርበታል።
ይሁን እንጂ ገቢ እያደገ ሲሄድ ለምን ከፍትሃዊነት እና ከቲኬት ተደራሽነት ጉዳዮች ባሻገር ፊፋ ከ4 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ትርፍ እንደሚያስፈልገው ጥያቄ ይፈጥራል። ይህም በ2019-22 መካከል ካለው ጠቅላላ ወጪ ከግማሽ በላይ ነው።
እንደ እውነቱ ከሆነ አሃዞቹ እንደሚያሳዩት ፊፋ በአንፃራዊነት አንዳንድ መሠረታዊ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ነገሮች በእጅጉ ቀንሷል።
በ2023-26 ውስጥ የውድድር በጀቱ ከ2.45 ቢሊዮን ወደ 5.62 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር አድጓል። ይህም ወደ 130 በመቶ የሚጠጋ ጭማሪ አሳይቷል። የልማት በጀቱ ደግሞ በ44 በመቶ ብቻ ጨምሯል። እናም የበጀት ገቢው ድርሻ ከ44 በመቶ ወደ 36 በመቶ ቀንሷል።
ፊፋ የወደፊት ዝግጅቶችን ወጪ ለመሸፈን እና የእግር ኳስ ልማትን ለመደገፍ ከፍተኛ ገቢ እንደሚያስፈልገው ሊከራከር ይችላል፤ ነገር ግን የፊፋ የ2027-2030 በጀት የተነገረው ሙሉ ታሪክ ይህ አይደለም።
አጠቃላይ ተጨማሪ ወጪዎች ወደ 3 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር አካባቢ ይገመታሉ። ውድድሮች እና ዝግጅቶችም ዋናው አንቀሳቃሽ ናቸው። ለ2019-2022 ልማት 44 በመቶ የወጪዎችን ድርሻ እንደሚይዝ ልብ ማለት ያስፈልጋል፤ ለ2023-2026 ይህ ወደ 36 በመቶ ቀንሷል። እና ለ2027-2030 ደግሞ ወደ 29 በመቶ እንደሚቀንስ ይገመታል።
እነዚህ አሃዞች ያለምንም ጥርጥር ይለወጣሉ። ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ ፊፋ ከእግር ኳስ ወይም ከማኅበራዊ ለውጥ ጋር የተያያዙ ሰፋ ያሉ ኢንቨስትመንቶችን ለመደገፍ ከቲኬት ሽያጭ የሚገኘውን ተጨማሪ ገቢ እንደሚጠቀም አያመለክቱም።
ምናልባት ይህ የሚያስገርም ላይሆን ይችላል፤ ምክንያቱም ፊፋ ከዚህ በፊት የአስተዳደር ተግዳሮቶች አጋጥሞታል። ከእነዚህም መካከል ሙስና፣ እጅ መንሻ መቀበል እና ማጭበርበር እንዲሁም ግልጽነት የጎደለው የሂሳብ አያያዝ ይገኙበታል።
እነዚህን ችግሮች ለማቃለል ማሻሻያዎች ተደርገዋል፤ እና ፊፋ እንደ ፊፋ ፋውንዴሽን ያሉ ፕሮግራሞችን ጀምሯል። ዓላማቸውም እግር ኳስን የሰዎችን ሕይወት ለማሻሻል መጠቀም ነው።
ይሁን እንጂ የፊፋን የኋላ ታሪክ ተመልክቶ ትርፍ እና ሀብትን አካትቶ መነሳት ያለበት በጣም አስፈላጊው ጥያቄ የፊፋ የፋይናንስ ዓላማዎቹን ለማሳካት ውጤታማ በሆነ መንገድ ጥቅም ላይ እየዋሉ ነው ወይ? የሚለው መሆን አለበት።
ፊፋ ዓላማውን "ጨዋታውን ማልማት፣ ዓለምን መድረስ እና የተሻለ የወደፊት ሕይወት መገንባት" በሚሉ ሐረጎች አጅቧቸዋል።