ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
BBC News, አማርኛ - ዜና
ዜና
ቀጥታ, ትራምፕ ከማክሰኞ በፊት ሆርሙዝ የማይከፈት ከሆነ ኢራን "ሲኦል" እንደምትሆን አስነዋሪ ቃላትን በመጠቀም ዛቱ
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራን ከማክሰኞ በፊት የሆርሙዝ ወሽመጥን የማትከፍት ከሆነ አገሪቱን “ሲኦል” እንደሚያደርጉ አስነዋሪ ቃላትን በመጠቀም አስጠነቀቁ።
ኤምሬትስ በጦርነቱ መያዟ በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ተጽእኖ ይቀንሰዋል? ሁቲዎችስ ለቀጣናው ምን ያህል ስጋት ናቸው?
በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ የጎላ ሚና ያላት ኤምሬትስ የኢራን ጥቃት ዋነኛ ዒላማ በመሆኗ ትኩረቷን እራሷን መከላከል ላይ አድርጋለች። ይህ ሁኔታ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል የተከሰተው ውጥረት ወደ ጦርነት እንዳያመራ አዘግይቶት ይሆን? ኢራንን ደግፈው ወደ ጦርነት የገቡት የየመን ሁቲዎች የቀይ ባሕር መግቢያን ለመዝጋት እየዛቱ ሲሆን፣ ይህ ሁኔታ ለኢትዮጵያ እና ለሌሎች አፍሪካ ቀንድ አገራት ምን ስጋት ይፈጥራል?
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናልን ይቀላቀሉ
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቪድዮዎች
ቪዲዮ, የእስራኤል ጥቃት ዋነኛ ዒላማ ሆኑት የኢራን ባለሥልጣናት
በኢራን ላይ ጥቃት ከተጀመረበት ደቂቃ አንስቶ እስራኤል አገሪቱን ከፍተኛ መሪዎች ዒላማ አድርጋለች። በዚህም ከጠቅላይ መሪው አንስቶ በርካታ ቁልፍ ባለሥልጣናት ተገድለዋል። ሳምንታትን ባስቆጠረው ጦርነት ምን ያህል የኢራን ከፍተኛ ባለሥልጣናት ተገደሉ?
ቪዲዮ, በሌሎች ጦርነቶች የተጋረደው የአይኤስ እንቅስቃሴ በሶማሊያ
ታጣቂው ቡድን አይኤስ በአፍሪካ በተለይም ሶማሊያዋ ፑንትላንድን ግዛት ውስጥ ይንቀሳቀሳል። ይህ ቡድን በሌሎች አገራት ያሉትን ቅርንጫፎቹን የሚቆጣጠረውም ከሶማሊያ ነው። ከተለያዩ አገራት ታጣቂዎችን በመመልመል እያሠለጠነ ወደ ቡድኑ ይቀላቅላል። የሌሎች ጦርነቶች መስፋፋት ደግሞ ቡድኑ በአፍሪካ እንቅስቃሴ ለማድረግ ምቹ ሁኔታን ፈጥሮለታል።
ቪዲዮ, አሜሪካ እና ሩሲያ አመሳስለው ስለሠሩት የኢራኑ ሻሂድ ድሮን ምን ይታወቃል?
ሻሂድ-136 የተባሉት ድሮኖች ከዒላማቸው ጋር በሚጋጩበት ጊዜ የሚፈነዱ ፈንጂዎችን ይዘው ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳሉ። እስካሁን በአሜሪካ ወታደሮች ላይ እጅግ የከፋው ጉዳት የደረሰው አንድ ድሮን በኩዌት የሚገኝ ጦር ሰፈርን መትቶ ስድስት የአሜሪካ ወታደሮች በመገደላቸው ነው። ለመሆኑ ይህ ድሮን እንዴት በመካከለኛው ምሥራቅ ፍርሃት ሊፈጥር ቻለ?
ቪዲዮ, የአራኑ ኃያል ሰው አያቶላህ ኻሜኒ ማን ናቸው? ሥልጣናቸውስ ምን ያክል ጠንካራ ነው?
ኃያሉ የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ እስራኤል እና አሜሪካ በቅንጅት በፈጸሙት ጥቃት መገደላቸው ተረጋግጧል። ከ35 ዓመታት በላይ ኢራንን የመሩት ኻሜኒ በእስላማዊ ሪፐብሊኳ ኢራን መንግሥት ውስጥ የነበራቸው ሚና እጅግ የጎላ ነበር። ጠቅላይ መሪው ከየት ተነስተው ምዕራባውያን በተለይ የአሜሪካ እና የእስራኤል ዒላማ አስከመሆን ደረሱ?
ቪዲዮ, ቱርክን ወደ ኦቶማን ዘመን ዝናዋ ለመመለስ የሚጥሩት ኤርዶዋን ምን እያደረጉ ነው?
ቱርክ ከኦቶማን ግዛተ መንግሥት መውደቅ በኋላ እንደ አገረ መንግሥት ከተመሠረተች 100 ዓመታት አለፋት። የቱርክ አባት በመባል የሚታወቁት አታቱርክ፣ አገራቸውን ከሃይማኖት ገለልተኛ እና ዘመናዊ እሳቤን እንድትላበስ መሠረት ጥለዋል። በዘመናዊው ዓለም መድረክ ጉልህ ተጽዕኖ ያላቸው የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶዋን እንደ ኦቶማን ዘመን ሁሉ ቱርክን በዓለም ኃያል ለማድረግ እየጣሩ ነው። ይሳካላቸው ይሆን?
ቪዲዮ, ኢትዮጵያ የባሕር በር “በባሌም ሆነ በቦሌ ማግኘቷ አይቀርም”- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር መንግሥታቸው ከኤርትራ ጋር ስለገባበት ቅራኔ አጀማመር ከዚህ በፊት ያልተናገሩትን ጉዳይ እማኞችን ጠቅሰው ተናግረዋል። በተጨማሪም በሁለቱ አገራት መካከል ለተፈጠረው መቃቃር ሌላ ምክንያት የሆነው የኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ፍላጎት “በባሌም ሆነ በቦሌ” የሚሳካ ነው በማለት በአርግጠኝነት ነው ተናግረዋል።
ቪዲዮ, ፕሬዝዳንት ትራምፕ ስለሕዳሴ ግድብ እስካሁን ምን አሉ?
ከቀናት በፊት በአባይ (ናይል) ጉዳይ ኢትዮጵያ እና ግብፅን ለማደራደር ጥያቄ ያቀረቡት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ ኢትዮጵያ የናይል ወንዝ "ፍሰትን የሚያስቆም ግድብ" ሠርታለች አሉ። በዚህም ምክንያት ግብፅ ከናይል ወንዝ "በቂ ውሃ እንደማታገኝ" የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ፤ ይህንን ጉዳይ "መፍታት ይኖርብኛል" ሲሉ ተደምጠዋል። ለመሆኑ ፕሬዝዳንቱ በተለያዩ ወቅቶች በጉዳዩ ዙሪያ ምን ተናገሩ?
ቪዲዮ, የቢሾፍቱ አየር ማረፊያ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ምን ማለት ይሆን?
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ አቅራቢያ 'አቡሴራ' በተባለ አካባቢ የሚገነባው አዲስ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ቅዳሜ ጥር 2/2018 ዓ.ም. መሠረተ ድንጋይ ተቀምጧል። 12 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር የሚወጣበት የአውሮፕላን ማረፊያ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ሲጠናቀቅ፣ በዓመት 60 ሚሊዮን መንገደኞችን ማስተናገድ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል። 3,500 ሔክታር መሬት የሚሸፍነው ይህ ግዙፍ የአውሮፕላን ማረፊያ አውሮፕላን ማረፊያ በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ ሲገባ በዓመት 110 ሚሊዮን መንገደኞችን ያስተናግዳል ተብሏል።
ቪዲዮ, ከፍተኛ የነዳጅ ሀብት ያላት አሜሪካ ለምንድን ነው በሌሎች አገራት ነዳጅ ላይ ዐይኗን የጣለችው?
አሜሪካ ከፍተኛ የነዳጅ ክምችት ቢኖረትም በሌሎች አገራት ውስጥ ባሉ የነዳጅ ክምችቶች ላይ ዘወትር ትረኩት ደታርጋለች። ለዚህ በበርካታ አገሮች ጦርነት ውስጥ በቀጥታ እና በተዘዋዋሪ ስትሳተፍ ቆይታለች። በቅርቡም በቬንዙዌላ ሰጥ ቀጥተኛ ወታደራዊ እርምጃ በመውሰድ መሪዋን ይዛ ወስዳለች። ከዚያም በኋላ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በቬንዙዌላ የነዳጅ ሀብት ላይ አሜሪካ ያላትን ፍላጎት በይፋ በተደጋጋሚ ሲናገሩ ተደምጠዋል።
አነጋጋሪ ጉዳይ
በኢትዮጵያ በኤሌክትሪክ መኪኖች ላይ የታየው 'የተጋነነ' የዋጋ መናር ከኢራን ጦርነት ጋር ይገናኛል?
የዓለም 20 በመቶ ነዳጅ መተላለፊያ የሆነው የሆርሙዝ ወሽመጥ በመዘጋቱ የተከሰተው የነዳጅ እጥረት በኢትዮጵያ ዋና ዋና ከተሞች የትራንስፖርት ዘርፍ ላይ ጫና ማሳደሩን ቢቢሲ ተመልክቷል። ከሰሞኑ ደግሞ በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ መኪና ዋጋ እስከ ግማሽ ሚሊዮን ብር መድረሱ ተሰምቷል። ይህ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ከኢራን ጦርነት ጋር ይያያዝ ይሆን?
ኤምሬትስ በመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት ከባድ ዋጋ እየከፈለች ያለችው ለምንድን ነው?
ኢራን አሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት ከከፈቱባት ቀን አንስቶ ከፍተኛውን ጥቃት ከእስራኤል ይልቅ በዙሪያዋ ባሉ አረብ አገራት ላይ ነው የፈፀመቸው። ከእነዚህም መካከል የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ዋነኛዋ የኢራን ጥቃት ዒላማ ሆና ዋጋ እየከፈለች ነው።
ብልጽግና ፓርቲ፤ የአብን እና የኢዜማ አመራሮች በሚወዳደሩባቸው የምርጫ ክልሎች ዕጩ አላቀረበም
ገዢው ብልጽግና ፓርቲ ዕጩ ባላቀረበባቸው ከ80 በላይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎች ውስጥ የተቃዋሚዎቹ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) እና የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) አመራሮች የሚወዳደሩባቸው የምርጫ ክልሎች እንደሚገኙ ቢቢሲ ተገንዝቧል።
በኢትዮጵያ የተለዩ የተሽከርካሪ የሠሌዳ ቁጥሮችን ለሚፈልጉ የጨረታ ጥሪ ቀረበ
በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች አዲስ የመለያ ሠሌዳ ቁጥር ለመስጠት የተዘጋጀው የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የተለዩ የሠሌዳ ቁጥሮችን በጨረታ ሊሰጥ ነው። ሚኒስቴሩ በመላው አገሪቱ የተሽከርካሪዎች የሠሌዳ ቁጥርን ለውጥ ለማድረግ የሚያስፈልገውን ዝግጅት ማጠናቀቁን እና በቅርቡም አዲሱን የሠሌዳ መለያ ቁጥር (ታርጋ) መስጠት እንደሚጀምር እስታውቋል።
ብልጽግና ፓርቲ ዕጩ ባላቀረበበት ትግራይ ክልል ምርጫ ይካሄዳል?
ብልጽግና ፓርቲ፤ ምርጫ የመካሄዱ ነገር አጠራጣሪ በሆነበት ትግራይ ክልል ለሚገኙ የፓርላማ እና የክልል ምክር ቤት መቀመጫዎች አንድም ዕጩ አለማቅረቡን ቢቢቢ የተመለከተው የዕጩዎች ዝርዝር ያሳያል። ስድስት ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሁለት ቅንጅቶች በበኩላቸው 101 ዕጩዎችን አስመዝግበዋል።
ባለፈው ምርጫ ብልጽግናን ከወከሉ የአዲስ አበባ ተመራጮች ውስጥ ከ60 በመቶ በላዩ በአዲስ ተተኩ
ብልጽግና ፓርቲ ግንቦት ላይ ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው ሰባተኛው አጠቃላይ ምርጫ ለአዲስ አበባ ከተማ ካቀረባቸው 154 ዕጩዎች ውስጥ 96 ያህሉ በባለፈው ምርጫ በመዲናዋ ያልተወዳደሩ እንደሆኑ ቢቢሲ ያደረገው ዳሰሳ ያሳያል። በመጪው ምርጫ በአዲስ አበባ ዕጩ ሆነው ካልቀረቡት ተመራጮች መካከል ምክትል ከንቲባው ጃንጥራር አባይ ይገኙበታል።
ፌደራል ፖሊስ የፊንቴክ መስራችን እና "ጥቅም በመጋራት" የተጠረጠሩ ታዋቂ ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ
የፊንቴክ ኢንቨስትመንት ድርጅትን "ባልተገባ" እና "በተጋነነ መልኩ" አስተዋውቀዋል እንዲሁም በሕገወጥ መንገድ ከተሰበሰበው ገንዘብ "ተጋሪ" በመሆን ተጠርጥረዋል የተባሉ ታዋቂ ግለሰቦች እና የማስታወቂያ ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር አውሎ ፍርድ ቤት ማቅረቡን የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ። የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዛሬ በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ላይ ባወጣው መግለጫ ከ1200 በላይ ዜጎችን አጭበርብረው የ1.7 ቢሊዮን ብር ጉዳት አድርሰዋል ያላቸውን የፊንቴክ ኢንቨስትመንት መስራች እና ባለቤቶች ላይ ምርመራ አጣርቶ አቃቤ ሕግ ክስ መመስረቱን ገልጿል።
ኢትዮጵያውያንን ጭምር እያሰለፈ ካለው አይኤስ ጋር የሚደረገው ፍልሚያ
ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ በእርስ በርስ ጦርነት እና ባለመረጋጋት ውስጥ በምትገኘው ሶማሊያ እየተፋለመችው ካለው የአገር ውስጡ አልሻባብ በተጨማሪ ዓለም አቀፍ ታጣቂ ቡድን እግሩን አስገብቷል። በአሁኑ ወቅት እስላማዊ መንግሥት (አይኤስ) ከተባለው የሽብር ቡድን ጋር እየተፋለመች ነው። ይህ ቡድን ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ አገራት ተዋጊዎችን እየመለመለ ያሰልፋል።
የኢንተርኔት ዳታን በመቆጠብ የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽን በቀላሉ ማንበብ ይፈልጋሉ?
የቢቢሲ አማርኛን ድረ ገጽ በቀላሉ በመክፈት ዜና እና ታሪኮችን በጽሑፍ ብቻ ያንብቡ!
የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት
በባሕረ ሰላጤው ጦርነት ውሃ እንዴት ከነዳጅ እኩል የግጭቱ አካል ሊሆን ይችላል?
የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት ከነዳጅ ሃብት ጋር ሊያያዝ እንደሚችል የሚገመት ጉዳይ ነው። አሜሪካ እና እስራኤል ከኢራን ጋር የሚያደርጉት ጦርነት እየተስፋፋ መሄዱን ተከትሎ ውሃም ሌላኛው የግጭቱ ማዕከል ሊሆን እንደሚችል እየተነገረ ነው። እንዴት?
የኢራን ሚሳዔሎች ወደ ታላላቆቹ የአውሮፓ ከተሞች ሊደርሱ ይችላሉ?
ኢራን በሕንድ ውቅያኖስ ዲያጎ ጋርሲያ ደሴት ላይ ወደሚገኘው የዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) እና የአሜሪካ የጋራ ወታደራዊ ሰፈር ላይ የረዥም ርቀት ባለስቲክ ሚሳዔሎችን ማስወንጨፏ በመካከለኛው ምሥራቅ ያለውን ግጭት እየተባባሰ መምጣቱን ያሳያል። በእርግጥ ሚሳዔሎቹ ወደታቀደላቸው ዒላማ ሳይደርሱ ቀርተዋል። ነገር ግን የእስራኤል የመከላከያ ሠራዊት ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ እንዲህ ዓይነት የረዥም ርቀት ሚሳዔሎች ጥቅም ላይ ሲውሉ ይህ የመጀመሪያው እንደሆነ ተናግሯል።
አሜሪካ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት በፈጸመችባቸው አገራት ምን ተከሰተ?
ዩናይትድ ስቴትስ በመካከለኛው ምሥራቅ ወደ ጦርነት ተመልሳለች። ዋሽንግተን በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ በቀጣናው በተካሄዱ ጦርነቶች ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት የተሳተፈች ሲሆን፣ ሁሉም ያመጡት ውጤት ላይ በአንድ ድምጽ ከስምምነት መድረስ አይቻልም። በተለይ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በመካከለኛው ምሥራቅ እና በሰሜን አፍሪካ ያደረገቻቸው ወታደራዊ ጣልቃ ገብነቶች ምን ውጤት አስገኙ?
አሜሪካ እና እስራኤል ብዙዎቹን የኢራን መሪዎችን ገድለዋል፤ ትራምፕ ከማን ጋር ሊደራደሩ ይችላሉ?
አንድ ወር ሊሞላው በተቃረበው ጦርነት ከሞላ ጎደል አብዛኞቹ የኢራን ቁልፍ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ መሪዎች ተገድለዋል። ነገር ግን ኢራን ከአሜሪካ እና ከእስራኤል ጋር የምታደርገውን ፍልሚያ እንዲሁም በመካከለኛው ምሥራቅ አገራት ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት ቀጥላለች። ከከባድ ውድመት እና የመሪዎቿ ግድያ በኋላ ኢራን በእነማን እየተመራች ነው?
የየመን ሁቲዎች በኢራን ጦርነት ውስጥ እንዳይሳተፉ የያዛቸው ምንድን ነው?
አሜሪካ እና እስራኤል ኢራን ላይ ጥቃት ከፍተው ቴህራን ያለአጋር ብቻዋን ሁለቱን ኃያላን እየተጋፈጠች ነው። በዚህ ጊዜ በኢራን የሚደገፈው እና በቀይ ባሕር ላይ ዋነኛ ስጋት የሆነው የየመኑ ታጣቂ ቡድን ሁቲ ባልተለመደ መልኩ እራሱን ያቀበ ይመስላል። እስራኤል በሐማስ ላይ ጥቃት ስትከፍት ፈጥኖ ምላሽ የሰጠው ሁቲ ኢራን ስትጠቃ ለምን ዝምታን መረጠ?
ኢራን ላይ የተከፈተው ጥቃት እንዴት መላውን ዓለም ሊያናጋ ቻለ?
ከተጀመረ ሁለት ሳምንታት ያለፉት "ኦፕሬሽን ኤፒክ ፊዩሪ" በመላው ዓለም ተጽዕኖ እየፈጠረ ነው። የኢራንን የባለስቲክ ሚሳዔሎች፣ የባሕር ኃይል እና የኒውክሌር ጦር መሣሪያ ምኞቷን ለማምከን ተብሎ የተጀመረው ዘመቻ አካባቢያዊ አለመረጋጋትን እና ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ተጽዕኖ እየፈጠረ ነው።
አሜሪካ እና እስራኤል፤ በኢራን ላይ ምን ዓይነት ሳይበር ጥቃቶች ፈጸሙ? ኢራንስ?
ወታደራዊ ጥቃት የመፈጸም ኃይልን የተመለከቱ ውይይቶች በሚነሱባቸው ወቅቶች አሜሪካ እና እስራኤል እንዴት ኢራንን እያጠቁ እንደሆነ በምሥል ጭምር ከማሳየት ወደ ኋላ አይሉም። በባለሙያ የተዘጋጁ ፎቶዎች እና ቪዲዮዎችን የሚጠቀመው የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ፤ ጥቅም ላይ እየዋሉ ያሉ የመሣሪያ፣ የጄት እና የመርከብ ዓይነቶችን የሚያሳዩ ልጥፎችን በየአጭር ሰዓት ልዩነት ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ይለጥፋል።
ከየፈርጁ
ጥልቅ እና በቂ እንቅልፍ ለማግኘት በቀን ውሏችን ማድረግ ያለብን አምስት ነገሮች
በእንቅልፍ እጦት ተቸግረዋል? በተቆራረጠ እንቅልፍ ምክንያት የተረበሸ ሌሊት ያሳልፋሉ? በዚህ ምክንያትስ የቀን ውሎዎ በድካም የተሞላ ነው? ጥናቶች ከእንቅልፋችን ስንነሳ ጥሩ ስሜት የመሰማቱ ምሥጢር የሚጀምረው ከቀን ውሏችን ነው ይላሉ።
ኦቲዝም ከሴቶች ይልቅ በተለይ በወንዶች ላይ ይስተዋላል? እንዴት ቀድሞ መለየት ይቻላል?
የዓለም ጤና ድርጅት በአውሮፓውያኑ በ2021 ባወጣው አሃዝ መሠረት በመላው ዓለም ከ127 ሰዎች መካከል አንዳቸው ኦቲዝም እንዳለበት/እንዳለባት ያሳያል። አነስተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገራት በቂ መረጃ ባይገኝም፤ ለአእምሮ ዕድገት መዛባት ያለው ተጋላጭነት በየአገሩ የተለያየ መሆኑ ተስተውሏል።
በዱባይ ውበት እና ሰላም ላይ ያጠላው የጦርነት ስጋት፣ የውጭ ዜጎች ምን እያሰቡ ነው?
ዱባይ ከተለያዩ አገራት የመጡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የውጭ ዜጎች መኖሪያ ናት። ከተማዋ ለአስርተ ዓመታት ሰላሙ በሚዋዥቀው ቀጣና ውስጥ የመረጋጋት እና የደኅንነት ተምሳሌት ሆና ታይታለች። በቅርብ ዓመታት ውስጥ ግጭቶች አብዛኛውን የቀጣናውን ክፍል መልክ ቢቀይሩም፤ ዱባይ በአብዛኛው ሳትነካ ቆይታለች። የኢራን ጦርነትን መጀመር ተከትሎ ግን ይህ ገጽታዋ ፈተና ውስጥ ወድቋል።
ብርሃኔ አስፋው፡ ለሴቶች ደኅንነት ባደረጉት ጥረት ለኖቤል ሽልማት እስከመታጨት የደረሱት ኢትዮጵያዊት
ብርሃኔ የመንግሥታቱ ድርጅት የሕፃናት ስምምነት ላይ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን የሚከለክሉ አንቀፆችን አርቅቀዋል፤ በስምምነቱ እንዲካተቱቱም ውትወታ አድርዋል። የሰብዓዊ መብት አርበኛ የሆኑት ወ/ሮ ብርሃኔ 60 ዓመታት የዘለቀ ስኬታማ ትዳርም አላቸው። ወ/ሮ ብርሃኔ አስፋው ለሴቶች ጤና እና ደኅንነት ላበረከቱት አስተዋፅኦ በሽልማት ተንበሽብሸዋል። ድርጅታቸውን አቋቁመው ከተለያዩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለማስቆም ሲታትሩ ያዩ ደግሞ ለኖቤል አጭተዋቸዋል። ቢቢሲ ወ/ሮ ብርሃኔን ስለ ሥራ እና ሕይወታቸው አነጋግሯቸዋል።
ቢቢሲ አማርኛን በዋትስአፕ ላይ ያግኙ
አጃኢብ!
ኖስትራዳመስ፡ የፈረንሳያዊው ኮከብ ቆጣሪ ትንቢቶች ለምን አሁንም ድረስ ተቀባይነት አገኙ?
በመቶዎች ከሚቆጠሩ ዓመታት በኋላ ደጋፊዎቹ ሁለቱንም የዓለም ጦርነቶች፣ የሂሮሺማ እና የናጋሳኪ የኒውክሌር ፍንዳታዎችን፣ የሂትለርን መነሳት እና የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ጨምሮ ብዙ ታሪካዊ ክስተቶችን፣ ምንም እንኳን እነዚህን ክስተቶች በስም ባይጠቅሳቸውም እንደተነበየ ይናገራሉ።
የኒውክሌር ጦርነት ሊያስነሳ የነበረው የኖርዌይ የአየር ሁኔታ ምርምር ሮኬት
በአውሮፓውያኑ ጥር 25/1995 ኖርዌይ 'ኖርዘርን ላይትስ' የተባለውን የሰማይ ላይ ደማቅ ብርሃን ለማጥናት የተኮሰችውን ሮኬት ሩሲያ በስህተት ወደ ሞስኮ የተወነጨፈ የኒውክሌር ሚሳዔል እንደሆነ ቆጥራው ነበር። ከቀዝቃዛ ጦርነት ስሜት ገና በቅጡ ያላገገመው ዓለም በአንድ የአዘቦት ቀን ለሰዓታት የቆየ በድጋሚ ጦርነት ውስጥ የመግባት አስከፊ ስጋት ተጋርጦባት ነበር።
የተመለሱ ጥያቄዎች
ፆም በሰውነታችን ውስጥ የሚያስከትለው ለውጥ እና የሚሰጠው ጥቅም ምንድን ነው?
ለእስልምና እና ለክርስትና እመነት ተከታዮች ዋነኞቹ የፆም ወቅት የሆኑት ረመዳን እና ዓቢይ ፆሞች ተጀምረዋል። የሁለቱም እምነቶነቶች ምዕመናን የፆሙን ጊዜ በየራሳቸው ሥርዓት እና ደንብ መሠረት የሚከውኑት ሲሆን፣ በየዕለቱ ለረጅም ሰዓታት ከምግብ እና ከውሃ ርቀው ይቆያሉ። በዚህ ጊዜ ታዲያ ፆም በሰውነት ላይ ምን ለውጥን ያስከትላል? ምንስ ጥቅም አለው?
"ተወዳጇ እና ደስተኛዋ ልጄ እንዴት በራሷ ላይ ወሰነች?" - በቲክ ቶክ እና በእኩዮቿ ጫና ራሷን ያጠፋቸው ኢትዮጵያዊት ታዳጊ
አቶ ነብዩ ማኅበራዊ ሚዲያ በታዳጊ ልጆች ላይ የሚያስከትለውን ተጽእኖ በተመለከተ መራራ የሆነ ልምድ ነው ያላቸው። የ13 ዓመቷ ልጃቸው ፊዮሬላ ላይ ምንም ዓይነት ምልክት ሳይመለከቱ በእኩዮቿ ጫና እና በማኅበራዊ ሚዲያ ግፊት ባላሰቡት ጊዜ ልጃቸው እራሷን አጥፍታ አግኝተዋታል።
ሌላ ዕይታ
ቢቢሲ አማርኛን በማኅበራዊ ሚዲያዎች ይከታተሉ
ከማኅደራችን
ማርበርግ ቫይረስ: የመጀመሪያው ታማሚ እና ሦስት መሪዎቿን ያጣችው የጂንካ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን
ከሌሊት ወፎች የሚነሳው የማርበርግ ቫይረስ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ከተገኘ አንድ ወር ሊደፍን ጥቂት ቀናት ቀርተውታል። የጤና ሚኒስቴር፤ እንዴት በሽታው በጂንካ ከተማ ሊነሳ እንደቻለ እስካሁን አልገለጸም። ለመሆኑ በጂንካ የመጀመሪያው ታማሚ ማን ነበር? የበሽታው መነሻ የሆኑት የሌሊት ወፎችን እና የመጀመሪያውን ታማሚስ ምን አገናኛቸው? ቢቢሲ ባደረጋቸው በርካታ ቃለ መጠይቆች ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ የሚሆኑ መረጃዎች አሰባስቧል።
"ቢገድሉኝ ይሻል ነበር"፡ የሴቶችን ሕይወት እያበላሸ ያለው የተዘነጋው የአማራ ክልል ጦርነት
ከሁለት ዓመት በላይ የሆነው በአማራ ክልል በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በሚካሄደው ግጭት ሰላማዊ ሰዎች ከባድ ዋጋ እየከፈሉ ነው። ግጭቱ በሰው ሕይወት እና በንብረት ላይ ከሚያደርሰው ጉዳት ባሻገር በሴቶች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት እና ሰቆቃ ትኩረትን አላገኘም። ቢቢሲ ለወራት ባካሄደው ክትትል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሴቶች የመደፈር እና የወሲባዊ ጥቃት ሰለባ መሆናቸውን መረጃ አግኝቷል።
በብርሌ ፍቅር የወደቁት ፈረንጅ 'ብርሌ ውስጥ የኢትዮጵያ ታሪክ አለ' ይላሉ
ሰሞኑን አረቄ ብሔራዊ አጀንዳ ሆና የማኅበራዊ ሚዲያ አናት ላይ ወጥታ ነበር። ጠጅ ቢሆን አናት ላይ አይወጣም፤ ወደ ጉልበት ነው የሚወርደው። ጠጅ ለመጨረሻ ጊዜ ጉዳይ ሆኖ የሥነ መንግሥቱ አናት ላይ ወጥቶ፣ 'ብሔራዊ አጀንዳ' የነበረው በዐፄ ዮሐንስ 4ኛ ዘመን ነው። ድሮ ጠጅ በብርሌ ይቀርብ ነበር። ከዚያ በብርሌ ይጠጣ ጀመር። ጠጅ ግን እንደ አረቄ ማንም ‘ተራ ዜጋ’ ብድግ አድርጎ አያንደቀድቀውም።ብርሌ ውስጥ የመደብ ታሪክ አለ። የዘመን ታሪክ አለ። የጭሰኛና የመሳፍንት ታሪክ አለ። ያልተሳከረ።
ዓለምን የሚዞረው ኢትዮጵያዊ ከዩቲዩብ ምን ያህል ያገኛል?
ከተከፈተ በዚህ ወር 20 ዓመት የሆነው የቪዲዮ ማጋሪያው የማኅበራዊ ሚዲያ መድረክ ዩቲዩብ ለብዙዎች የተለያዩ አጋጣሚዎችን ፈጥሯል። ከእነዚህም መካከል አቤል ብርሃኑ አንዱ ነው፤ በዩቲዩብ አማካኝነት 62 ሀገራትን ዟሯል። ያልረገጠው አህጉር አንታርቲካን ብቻ ነው። ሁሉንም የአሜሪካ ግዛቶች አካሏል። ከዘጠኝ ዓመታት በላይ ዩቲዩብ ላይ የቆየው አቤል ከዩቲዩብ ምንያህል ያገኛል?
ቪዲዮ, በአርሰናል ‘ፍቅር የወደቁት’ የ65 ዓመቷ እናት፡ ወይዘሮ እቴቱ ማሞ, ርዝመት 3,29
ከእንግሊዝ ታላላቅ ቡድኖች መካከል አንዱ የሆነው የአርሰናል የልብ ደጋፊ የሆኑት ወ/ሮ እቴቱ ማሞ የ65 ዓመት እናት ናቸው። ላለፉት 20 ዓመታት አርሰናልን ያለማቋረጥ ደግፈዋል። እንደብዙዎቹ የቡድኑ ደጋፊዎች ዘንድሮ አርሰናል ዋንጫ ባለማንሳቱ ቢከፉም ድጋፋቸው ግን እንደሚቀጥል ይናገራሉ። ከሁሉም ተጫዋቾች ይልቅ እሳቸው ገብረኢየሱ ለሚሉት ለጋብሬል ጀሱስ እና ለቡካዮ ሳካ የተለየ ፍቅር አላቸው።
እነ ሞገስ አስገዶም፣ አብረሃ ደቦጭ፣ ፕ/ር አስራት ወልደየስ፣ ፕ/ር መስፍን ወ/ማሪያም፣ ስብሐት ገ/እግዚአብሔር የተማሩበት ተፈሪ መኰንን
ተፈሪ መኰንን ትምህርት ቤት ታሪክ የዘመናዊት ኢትዮጵያ ንድፍ እንደማለት ነው። ላለፉት 100 ዓመታት ታላላቅ ሰዎችን ወልዷል። ለመኾኑ ይህ ተማሪ ቤት እነማንን አፈራ? ይህ ሐተታ በ100 ዓመት ታሪኩ ውስጥ በአንድም ሆነ በሌላ አሻራቸውን ያሳረፉትን ግለሰቦች ያወሳል፤ ከካናዳዊያን ጄስዊቶች እስከ ከንቲባ አዳነች አበቤ፤ ከቱጃሩ ራስ ኃይሉ ተክለሃይማኖት እስከ ቢሊየነሩ ሼክ አላሙዲን፣ ከሐኪም ወርቅነህ እሸቴ እስከ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ።
ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት የምትገኘው አሊ ዶሮ እና አካባቢዋ ለምን የእገታ ማዕከል ሆኑ?
ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ በሕዝብ እና በጭነት ተሽከርካሪዎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች እና እገታዎች ተበራክተዋል። ይህ ክስተት ደግሞ ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው የሰሜን ሸዋ አካባቢ በተደጋጋሚ ሲከሰት ቆይቷል። በተለይ አሊ ዶሮ የሚባለው ቦታ የጥቃት እና የእገታ ማዕከል ሆኗል እየተባለ ነው። ቢቢሲ በተለይ ይህ ቦታ ለምን የመንገደኞች እና የአሽከርካሪዎች ‘የሞት ቀጣና’ ሆነ? በሚል ለወራት የዘለቀ ምርመራ አድርጓል።
ባይተዋር ከተማ፡ “ፒያሳ፣ ካዛንቺስ... ሰፈሬ አልመስል አሉኝ”
ባለፉት ዓመታት በአዲስ አበባ በቅርስነት ተመዝግበው የነበሩ እንዲሁም ሌሎችም ታሪካዊ ሕንጻዎች፣ ቤቶች እና አካባቢዎች እንደ ዋዛ አፈር ለብሰዋል። በዚህ ዘገባ፣ አንድን ሕንጻ ወይም ቤት ቅርስ አልያም ታሪካዊ ሥፍራ ለማለት መስፈርቱ ምንድን ነው? የታሪካዊ ሕንጻዎች እና ቤቶች መፍረስ በታሪክ፣ በነዋሪዎች ሥነ ልቦና፣ በኪነ ሕንጻ እና በማኅበራዊ መስተጋብር ላይ ምን ጫና ያሳድራል? ቅርሶች እና ታሪካዊ ሥፍራዎችን እንዴት ጠብቆ ማደስ፣ ማዘመን፣ መልሰው አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ማድረግ እንዲሁም ከሌሎች ግንባታዎች ጋር ጎን ለጎን እንዲሄዱ ማድረግ ይቻላል? የሚሉት እና ተያያዥ ነጥቦች ተዳስሰዋል።
“ሰው መሃል ሆኜ ሁሉም ጨካኝ ሆኖብኝ ነበር” - የፀጋ በላቸው ዘጠኝ የጠለፋ ቀናት
ግንቦት 2015 ዓ.ም. የተፈጸመው የፀጋ በላቸው ጠለፋ ብዙዎችን ያስቆጣ፣ መነጋገሪያም የሆነ የወንጀል ድርጊት ነበር። ፀጋ፤ ከአንድ ዓመት ከመንፈቅ በፊት ተጠልፋ ያሳለፈቻቸውን ቀናት በተመለከተ ለመጀመሪያ ጊዜ ለቢቢሲ በዝርዝር ተናግራለች። ከቢቢሲ ጋር በነበራት ዘለግ ያለ ቆይታ፤ ስለተጠለፈችበት መንገድ እና ስላሳለፈቻቸው ዘጠኝ ቀናት በዝርዝር ተርካለች። ከጠለፋው ነጻ የወጣችበት መንገድም አስቀድሞ በክልሉ መንግሥት ከተገለጸው የተለየ እንደሆነ ለመጀመሪያ ጊዜ ተናግራለች። ለምን ከኢትዮጵያ እንደተሰደደች እና ስለ ቀጣይ ዕቅዶቿም እንዲሁ አጋርታለች።
". . . ከምድሩ ይልቅ የሰማዩን መንገድ ለመምረጥ ተገደናል" እገታ ያሰጋቸው መንገደኞች
ባለፉት ዓመታት በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ውስጥ የሚካሄዱ ግጭቶች እና በታጣቂዎች የሚፈጸሙ እገታዎች ዜጎች በፈለጉት ጊዜ እና መንገድ በአገሪቱ ውስጥ እንዳይንቀሳቀሱ ብርቱ ስጋት ፈጥሮባቸዋል። በተለይ ደግሞ የመንገደኞች ማጓጓዣ ተሽከርካሪዎችን በማድረግ የሚፈጸሙት ያላባሩ እገታዎች በዋነኞቹ የአገሪቱ ክልሎች ውስጥ እንቅስቃሴን አዳጋች አድርገውታል። በዚህም ሳቢያ አቅሙ ያላቸው እና የግድ የሆነባቸው ሰዎች ፊታዎችን ወደ አየር ትራንስፖርት አዙረዋል።
"'ቁርጭምጭሚት' የሚለው ቃል ያስቀኛል'' ለ23 ዓመታት ለፈረንጆች አማርኛን ያስተማረችው ፖላንዳዊት፣ ዶ/ር ኤቫ ቮልክ-ሶሬ
ፓላንዳዊቷ ዶ/ር ኤቫን የአማርኛ ቋንቋን ከ40 ዓመት በፊት ተምራ በዲግሪ ከተመረቀች በኋላ ከሃያ ዓመታት በላይ በማስተማር በርካቶችን በአማርኛ ቋንቋ ዲግሪ አስይዛለች። የምታስተምርበት ዩኒቨርስቲ ወደ 80 ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ አማርኛን እያስተማረ ነው። አማርኛ ቋንቋን “ፏፏቴ ነው” የምትለው ዶ/ር ኤቫን በአገሯ በአማርኛ አስተርጓሚነት ትሠራለች። ለመሆኑ እንዴት ከአማርኛ ጋር ተዋወቀች?