ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
የማህጸን ካንሰርን ያጠፋች የመጀመርያዋ አገር ለመሆን ጥድፊያ ላይ ያለችው አውስትራሊያ
ክሪስሲ ዋልተርስ ልጅ ለማግኘት ረዥም ዓመት ጥረት ካደረገች በኋላ ብትወልድም በስድስት ወሯ ልጇ ያለእርሷ እንደምታድግ ተነገራት።
በወቅቱ 39 ዓመቷ ላይ የነበረችው ዋልተርስ ከፍተኛ ደም ይፈስሳት ጀመር።
ምክንያቱን ለማወቅ በተደጋጋሚ ሆስፒታል ከተመላለሰች በኋላም ምርመራ ተደርጎላት ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰ የማህጸን ካንሰር መታመሟ ተነገራት።
"ለባለቤቴ ኒል… ትልቅ ስህተት ተሰርቷል ስል ነገርኩት" ስትል ዋልተርስ ታስታውሳለች።
ይህ ከሆነ ከአስርት ዓመታት በላይ አልፎታል። ካንሰሩ ወደ ሌሎች የአካል ክፍሏ ተዛምቷል። ዶክተሮች ካንሰሩ ገዳይ መሆኑን ነግረው ተስፋ አስቆረጧት።
"ለጠላቴ እንኳን ይህንን አልመኝም" ስትል በወቅቱ የተሰማትን ትገልጻለች።
አሁን የ12 ዓመት ታዳጊ የሆነችው ልጇ ሕመሙ የሕይወቷ አካል ሆኖ ኖራለች። ዋልተርስ ልጇ ከሦስት ዓመቷ ጀምሮ ስለሞት እየተወራ ማደጓን ትገልጻለች። በቤተሰቡ መካከል በግልጽ ስለበሽታው በመነጋገር ማደጓን ትናገራለች።
ነገር ግን እአአ በ2026 አውስትራሊያ እናቷን አንድ ቀን የሚገድለውን በሽታ ለማጥፋት ክትባት ስትጀምር ተከተበች።
አውስትራሊያ በሚቀጥሉት አስር ዓመታት ውስጥ በሽታውን ለማጥፋት አቅዳ እየሰራች ነው። አውስትራሊያ ካንሰርን ያጠፋች የመጀመርያዋ የዓለማችን አገር ለመሆን ጥድፊያ ላይ ናት።
በሽታውን ለማጥፋት ሁለት የተለያዩ መንገዶች
በአውስትራሊያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የ12 እና የ13 ዓመት ሕጻናት ተቀምጠው አንድ በአንድ እየተነሱ ክትባታቸውን ይከተባሉ።
ነርሷ መርፌው የሚያማቸው ለቅጽበት ብቻ መሆኑን እየገለጸች ታረጋጋቸዋለች።
ከደቂቃዎች በኋላ ተከትበው ወደ ክፍላቸው ይመለሳሉ።
ይህ በአገር አቀፍ የክትባት ፕሮግራሙ ውስጥ ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የተዘጋጀው ሦስት ዙር ክትባት አካል ነው።
ክትባቱ ኤችፒቪን ያካትታል። የኤችፒቪ ክትባት የተለያዩ ዓይነት የኤችፒቪ በሽታዎችን ይከላከላል።
ይህም የማህጸን ካንሰር፣ የመቀመጫ ካንሰር፣ የመራቢያ አካላት ካንሰር እና የአንገት ካንሰርን ይጨምራል።
ምንም እንኳ ኤችፒቪ ምልክት ባይኖረውም እና ያለምንም ሕክምና ሊድን ቢችልም አንዳንድ ዝርያዎች ግን ወደ ማህጸን በር ካንሰርነት ያድጋሉ።
ይህ በመላው ዓለም ሴቶች ከሚያጋጥሟቸው ካንሰሮች መካከል በአራተኛ ደረጃ የተቀመጠ ነው።
እንደ ዕድል ሆኖ ጥቂት ካንሰር አምጪ ከሆኑት ቫይረሶች መካከል ሲሆን በክትባት መከላከል ይቻላል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚደረገውን የማህጸን በር ካንሰር ቁጥጥርን የሚመሩት ካረን ካንፌል የበሽታው ተጽዕኖ በአውስትራሊያ እና በቀሪው ዓለም ላይ መሆኑን ያብራራሉ።
ፕሮፌሰሯ "ሁሉም ሰው በማሕጸን በር ካንሰር የተጠቃ እናት ወይም እህት ወይም አያት አለው" ይላሉ።
ነገር ግን እአአ በ2026 በዩኒቨርስቲ ኦፍ ክዊንስላንድ አንድ ፈር ቀዳጅ የሆነ ክትባት ተገኘ።
ላለፉት አስርት ዓመታት የአውስትራሊያ ተመራማሪዎች ጋርዳሲል ሲሉ የሰየሙትን ክትባት መስራት ችለዋል።
እህ ክትባት በመድሃኒት ቄትጥር ባለሥልጣን ፈቃድ ያገነ ሲሆን ኤችፒቪን ለመከላከል ያገለገልላል.
ከአንድ ዓመት በኋላም አውስትራሊያ በመላው አውስትራሊያ ክትባቱን የሰጠች የመጀመርያዋ አገር ሆናለች።
ክትባቱ ለዓለም አቀፍ የጤና ባለሙያዎች ካንሰር የሌለበት ዓለም ሊኖር ይችላል የሚል ተስፋ ሰጥቷቸዋል።
በካንፌል እና የዓም ጤና ድርጅት እገዛ ይህ እንዴት ሊሆን እንደሚችል ለመረዳት እየሞከሩም ነው።
ካንፌል የአውስትራሊያ የማኅበረሰብ ጤና ስኬት ለሌሎች አገራት ምሳሌ መሆን እንደሚችል ለማሳየት ከዓለም ጤና ድርጅት ጋር ይሰራሉ።
በአውስትራሊያ እአአ በ2013ቱ ሰፊ የክትባት መርሃ ግብር የተካሄደ ሲሆን ወንዶች የቫይረሱ ተሸካሚዎች ሊሆኑ ስለሚችሉ እንዲካተቱ ተደርጓል።
እአአ በ2017 ደግሞ በኤችፒቪ አማካኝነት የሚመጣ ካንሰርን ለመለየት የተሸሻሻሉ የምርመራ ዘዴዎችን መጠቀም ጀምራለች።
አገሪቱ ሴቶች ራሳቸው ናሙና የመውሰድ አማራጭን ከሰጡ የመጀመሪያዎቹ አገራት መካከል አንዷ ነበረች።
አውስትራሊያ በትክክለኛው ጎዳና ላይ ናት?
የማሕጸን በር ካንሰርን እንደ የሕዝብ ጤና ችግር ጠፋ ማለት ከአውስትራሊያ ጨርሶ ጠፋ ማለት አይደለም። ተመራማሪዎች አንድን በሽታ "ጠፍቷል" የሚሉት ከ100ሺህ ሰዎች መካከል ከአራት ሰዎች በታች ብቻ ሲያዙ ነው።
ባለሙያዎች አገሪቱ በ2035 ካንሰርን ለማስወገድ ያቀደችውን ግብ ለማሳካት በትክክለኛው መንገድ ላይ መሆኗን የሚገልጽ ሪፖርት አውጥተዋል፤ እና ምናልባትም ቀደም ብሎ ሊሳካ ይችላል።
እአአ ከ1982 ዓ.ም ጀምሮ ሲታይ በአውስትራሊያ የማሕጸን ካንሰር የመያዝ እና የሞት መጠን በግማሽ ቀንሷል።
በ2021 የተሰበሰቡ መረጃዎች ደግሞ ለመጀመርያ ጊዜ እድሜያቸው ከ25 ዓመት በታች በሆኑ ወጣቶች ላይይ የማሕጸን በር ካንሰር አልተገኘም።
"እስካሁን ድረስ በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሁሉም ሴቶች አይደሉም፣ ነገር ግን ይህ የማስወገድ ጽንሰ ሀሳብ እውን እየሆነ መሆኑን ማየት ይችላሉ" ብለዋል ካንፌል።
አውስትራሊያ በአሁን ወቅት ከ100ሺህ ሴቶች መካከል 6.3 አዳዲስ ታማሚዎች ይገኛሉ። ከ15 ዓመት በታች ላሉ ሴቶች የሚሰጠው ክትባት 80 በመቶ ደርሷል።
የበለጠ ተጋላጭ በሆነ የእድሜ ክልል ላይ የሚገኙ ሴቶች ደግሞ 85 በመቶዎቹ የማሕጸን በር ካንሰር ምርመራ አድርገዋል።
ይህንን ወደ ቀሪው ዓለም ወደ መካከለኛ እና ዝቅተኛ ገቢ ወዳላቸው አገራት ለማስፋፋት ዋናው ተግዳሮት ገንዘብ ነው።
ካንፌል እና ቡድናቸው መንግሥታት በማሕጸን በር ካንሰር ላይ ገንዘባቸውን ቢያውሉ አዋጭ መሆኑን ለማሳመን እየጣሩ ነው።
ሕይወትን ከማዳን እና "አስደናቂ የማህበራዊ ተፅእኖ" ከማሳረፍ ባለፈ፣ ሴቶች አምራች የሆን ሐራተኛ አካል ሆነው ሊቀጥሉ እና የኢኮኖሚ ምርታማነት ሊጨምር ይችላል ሲሉ ካንፌል ተናግረዋል።
አክለውም ምንም እንኳ በመከላከል ላይ የሚውል መዋዕለ ነዋይ ተመላሽ እንደሚሆን ማስረጃዎች አሉ ሲሉ ሃሳባቸውን ያጠናክራሉ።
አውስትራሊያ ከመንግሥተ እና ከለጋሾች በምታገኘው ገንዘብ ጎረቤቶቿን ቫናቱ እና ፓፓዋ ኑው ጊኒን ክትባቱን በማቅረብ እየደገፈች ነው።
ይሁን እንጂ የኤችፒቪ ክትባትን ለዝቅተኛ ገቢ ላላቸው አገራት የሚያቀርብ የውጭ ድጋፍ መቋረጥ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል።
እአአ በ2025 መጋቢት ወር የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለታዳጊ አገራት ክትባት በማቅረብ ረገድ የሚደረገውን ድጋፍ አቋረጡ።
"ግልጽ የሆነውን ለመናገር፣ ከፍተኛ ገቢ ባለበት አገር ውስጥ በመኖራችን እድለኞች ነን፤ ዓለም አቀፍ የጤና አጠባበቅ እና ለሁሉም ተደራሽ የሆነ አገልግሎት አለን" ይላሉ ካንፌል።
ዓለም አቀፍ ተጽዕኖ
ዋልተርስ የማሕጸን ካንሰር ከፍተኛ ዋጋ የሚጠይቅ 'የሙሉ ጊዜ ስራ" ነው ብላለች። ረፍት የለሽ ሕክምና ቀጠሮ፣ በርካታ የጎንዮሽ ጉዳት፣ የፋይናንስ ጫና ከተጽዕኖዎቹ መካከል ናቸው።
ነገር ግን እርሷ ያለፈችበት ለሌሎች ተስፋን የሰጠ መንገድ ሆኗል።
"በአንዳንድ አገሮች መካከል ማን ቀድሞ እንደሚያሸነፍ የሚገልጽ በጎነት የተሞላበት፣ ምናልባትም ፉክክር እየፈጠረ ነው" ይላሉ ካንፌል።
ስዊድን እና ሩዋንዳ ሁለቱም በ2027 የማኅጸን ካንሰርን ለማስወገድ ከፍተኛ ግቦችን አስቀምጠዋል።
ምንም እንኳን ሁለቱም አገሮች ከግባቸው ወደኋላ ቢቀሩም የተፋጠነ የክትባት እና የምርመራ ፕሮግራሞችን ጀምረዋል።
ዩኬ በ2040 የማኅጸን ካንሰርን ለማጥፋት ግብ ብታስቀምጥም ነገር ግን የኤችፒቪ ክትባትም ሆነ የማኅጸን ካንሰር ምርመራ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በጣም ቀንሷል።
ካንፌል አፅንዖት እንደሚሰጡት እንደ ኤችአይቪ መከላከል ያሉ ተላላፊ በሽታዎችን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ እጅግ በጣም ጥሩ ምሳሌዎች ቢኖሩም የማኅጸን ካንሰርን ለማከም የሚደረገው አቀራረብ ልዩ እና እውነተኛ ዓለም አቀፍ ጥረት ነው።
"የዓለም ጤና ድርጅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ካንሰርን እናስወግዳለን ያለው ለመጀመሪያ ጊዜ ነው" ይላሉ ካንፌል።
"ይህ በእውነቱ ለካንሰር አዲስ ፅንሰ ሀሳብ ነው።"