ለመፀነስ የሚፈልጉ ሴቶችን የሚያጭበረብሩ እና ለአደጋ የሚያጋልጡ የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች

ታትሟል
የንባብ ጊዜ: 6 ደቂቃ

ወላጆች ለመሆን አጥብቀው የሚሹ ሴቶች በድረ ገፆች የወሲብ ትንኮሳ እና ርካሽ፣ ሕጋዊ ያልሆነ የወንድ ዘር ፍሬ እየቀረበላቸው ነው።

የወሊድ (ፈርቲሊቲ) ሕክምና ማግኘት ያልቻሉት በማኅበራዊ የትስስር ገፆች አማራጭ እየፈለጉ ነው። በዚህም ቁጥጥር የሌለበት ገበያ የፈጠረ ሲሆን፤ የወንድ ዘር ፍሬ ፈላጊዎችን እና ለጋሾችን በቀላሉ የሚያገናኙ ድረ ገፆችም እንዲያማትሩ አድርጓቸዋል።

ቢቢሲ ዌልስ 100 ፓውንድ በመክፈል በሚቀጥለው ቀን በድረ ገጽ አማካኝት በቲማቲም ድልህ ጣሳ ተደርጎ አንድ እሽግ ተልኮለታል።

የዩናይትድ ኪንግደም የወሊድ (ፈርቲሊቲ) ተቆጣጣሪ ሴቶች "በአደገኛ የዘር ፍሬ በዝባዦች" አደጋ ላይ ናቸው ብሏል።

ቢቢሲ ለምርመራ ዘገባው በድረ ገፅ የወንድ ዘር ፍሬ ማግኘት ምን ያለል ቀላል እንደሆነ ለማሰስ ባደረገው ሙከራ አገልግሎቸታውን የሚሰጡ ወንዶች እጥረት አልነበረም።

የአንድ ድረ ገፅ ማስታወቂያ 'ጆ ዶነር' [ለጋሹ ጆ] ከሚባል ሰው አስተማማኝ የዘ ርፍሬ በፖስታ ቤት በኩል "በአስተማማኝ" ሁኔታ እንደሚቀርብ ይገልጻል።

'ፍሬያማ ለጋሽ' ተደርጎ የቀረበው ጆ በመላው ዓለም በግብረ ሥጋ ግንኙነት እና በሕክምና እርዳታ 180 ልጆች እንዳሉት ይገልጻል።

በዌልስ ዋና ከተማ ካርዲፍ የቤተሰብ ፍርድ ቤት ዳኛ ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ የዘር ፍሬ ልገሳን አደጋ ለማስጠንቀቅ ግለሰቡ ሮበርት አልበን እንደሚባል ይፋ አድርገዋል።

ቢቢሲ ትክክለኛ ባልሆነ ስም ከሁለት የኢሜል እና አንድ አጭር የስልክ ለውውጥ በኋላ በሚቀጥለው ቀን የዘር ፍሬውን እንዲያደርስ አመቻቸ። ማን እንደሆንን ለማረጋገጥ እና የጤና ምርመራ ውጤትን እንድንመለከት አላደረገም።

በቲማቲም ድልህ ካርቶን በአንድ ሲሪንጅ የወንድ የዘር ፍሬ ላለከልን 100 ፓውንድ በጥሬ ገንዘብ አስከፈለን።

ፈቃድ ያለው ክሊኒክ የዘር ፍሬው በደረሰን በአራት ሰዓት ውስጥ ባደረገው ምርመራ የዘር ፍሬው ሁሉም ህዋሳት መሞታቸውን አረጋግጧል።

አልበን የዘር ፍሬውን እንዴት እንዳስቀመጥነው እና እንዳዘዋወርነው ጠይቀን። በማድረስ ሂደቱ አብዛኛውን ጊዜ ለመፀነስ የሚያስችሉ በቂ የዘር ፍሬ እንደሚገኝ እና በዚህ መንገድ "በርካታ ስኬታማ እርግዝናዎች" እንዳሉ ለው።

አልበን እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ሌሎች ወንዶች የዘር ፍሬ ከሚፈልጉ ሴቶች ጋር ለመገናኘት ፌስቡክን ተጠቅመዋል። አንዳንድ የፌስቡክ ቡድኖች እስከ 40 ሺህ የሚደርሱ አባላት አሏቸው።

የመለያ ምሥል የሌለው ያለው የለጋሽ ቡድን ተቀላቀልኩ። ከአንዳንድ እውነተኛ ከሚመስሉ የመልዕክቶች ልውውጥ በኋላ ብዙዎቹ የወሲብ ጥያቄ ወይም የወንድ ዘር መሸጫ ዋጋን፣ የእርቃን ፎቶዎችን ይጠይቃሉ፤ እንዲሁም በተደጋጋሚ ለመገናኘት ቀጠሮ ለመያዝ መልዕክት ይልካሉ።

አንዳንድ ወንዶች ያለማቋረጥ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ለመፈፀም ይገፋፋሉ፤ ይህም በጣም ርካሹ እና በጣም ውጤታማው አማራጭ እንደሆነ ሊያሳምኑ ይሞክራሉ።

አንዲት ሴት በሰሜን ዌልስ ከሚኖር አንድ ወንድ ልገሳ እንደተቀበለች እና ከዚያም በወንጀል የተፈረደበት የወሲብ ወንጀለኛ መሆኑን አውቃ አስጠንቅቃለች።

የወሊድ እና የፅንስ ሕክምና ባለሥልጣን ቁጥጥር ያልተደረገበት ልገሳ በባለሥልጣኑ ፈቃድ ካለው ዓውድ ውጪ የሚከናወን ልገሳ እንደሆነ ይገልፃል። ይህም በዩኬ ውስጥ የወንጀል ድርጊት እንደሆነ ያክላል።

የደቡብ ዌልስ ነዋሪ የሆኑት ቲና እና ባለቤቷ ኒኪ ቁጥጥር ያልተደረገበት የዘር ፍሬ ልገሳ ላይ ዓይናቸውን ጥለዋል። የጤና መድኅኑ ለሚያቀርበው የገንዘብ ድጋፍ ብቁ ባለመሆናቸው የግል ሕክምና በጣም ውድ ሆኖ ተሰማቸው።

"እናት መሆን እንደምፈልግ ሁሌም አውቅ ነበር። ከቤተሰባችን የሆነ ነገር እንደጎደለ እናውቃለን" ትላለች ቲና።

ስለ አደጋዎቹ እንደምታውቅ እና ከለጋሾች የሚመጡትን ማንኛውንም ጫና እንደምትጠነቀቅ አክላለች።

"ድረ ገፅ አለ፣ ልክ እንደ ምርጫ ዝርዝር እና ቲንደር [የፍቅር አገናኝ መተግበሪያ] ድብልቅ ነው" ትላለች ቲና።

የተመሳሳይ ፆታ ጥንዶቹ በሰው በሠራሽ መንገድ ለመፀነስ ቢፈልጉም፤ ወንዶች ግን ብዙውን ጊዜ ወሲብን እንደ ምርጥ አማራጭ አድርገው ይመክሯቸዋል።

"እኔ እና ባለቤቴ እርስ በርስ መረዳዳታችን በጣም ጠቃሚ ይመስለኛል። ስለዚህ ማንም ሰው ማድረግ የማንፈልገውን ነገር እንድናደርግ ጫና ሊያሳድርብን የሚችልበት ምንም መንገድ አልነበረም። ምክንያቱም ልጅ ብቻ መውለድ የምትፈልጉት ከሆነ በጣም ተጋላጭ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ናችሁ።"

ቲና እና ኒኪ በመጨረሻ ልጅን በጋራ ማሳደግ የሚፈልጉ ሰዎች መገናኛ በሆነ ድረ ገፅ ላይ ደኅንነት የተሰማቸውን ለጋሽ አገኙ። እና ሁሉንም ወገኖች የሚያስማማ ውል አስረዋል።

ግን ይህ ሕጋዊ ውል አይደለም።

"ወደፊት መጥቶ የወላጅነት መብቶችን መጠየቅ እና ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ሊወስድ የሚችልበት ዕድል አሁንም አለ" ትላለች ቲና።

"ነገር ግን ይህን ለማስቆም በተቻለን መጠን ብዙ ነገሮችን አስቀምጠናል ብዬ አስባለሁ። እና ይህን በእኛ ላይ በፍፁም ያደርጋል ብዬ በእውነቱ አላምንም።"

አሁን የአንድ ዓመት ልጅ አላቸው።

"ለረጅም ጊዜ ፈልገነው [ልጅ] ነበር። በግልፅ ማየት እንደሚቻለው አደጋ እንዳለው ተረድተን ነው የገባንበት፤ ግን የሚገባው ነው።"

ቁጥጥር ያልተደረገባቸው ለጋሾች አገልግሎት የሚሰጡበት የተለየ መንገድ አላቸው። በነፃ ወሲብ ከሚፈፅሙት ጀምሮ እስከ በሰው ሠራሽ መንገድ ለመፀነስ ወጪያቸው ተሸፍኖ ከዓለም ዙሪያ የሚመጡትን ያካትታል።

የ25 ዓመቱ ዳንኤል ባየን በአሜሪካ የሚኖር ሲሆን በ2025 በሰው ሠራሽ መንገድ የዘር ፍሬ ለመለገስ ወደ እንግሊዝ ተጉዟል። ዳንኤል ይህ ጉዞ አራት ሕፃናትን እንዳስገኘ ተናግሯል።

ቢቢሲ ከዳንኤል ጋር ሦስት ቀናትን አሳልፏል። ዳንኤል በሠራቸው ቪዲዮዎች ላይ "ከፍተኛ ተከፋይ ለጋሽ" እንደሆነ እና "ለትርፍ ያልሆነ" ሥራ እንደሚሠራ ተናግሯል።

"[የዘር ፍሬ] ተቀባዮች ጉዞዬን ብቻ ሳይሆን የጤና እና የኑሮ ወጪዎቼን መሸፈን አለባቸው" ይላል።

በዩኬ ደንበኞቹ የጉዞ ወጪውን ብቻ እንዲሸፍኑ ብቻ እንደጠየቀ ተነግሮ፤ በሌላ አካባቢ ግን ለልገሳው እስከ 20 ሺህ ዶላር እንደቀረበለት ይገልፃል።

ቢቢሲ ገንዘብ ሊኖራቸው የሚችሉ ሰዎችን መጠቀሚያ ስለማድረጉ ሲጠይቀው፤ "ሌሎች ሰዎች ምን እንደሚያስቡ ግድ የለኝም። ለልጆቹ እና አብሬያቸው ከምሠራ ቤተሰቦች ጋር የሚስማማውን ነገር ላይ እጨነቃለሁ" ይላል።

ዳንኤል ራሱን "ለሁሉም ክፍት የሆነ ለጋሽ" ብሎ ይጠራል። ​​ልጆች ማንነቱን በማወቃቸው ደስተኛ ነው። ስለ አኗኗሩ እና ስለ ጤና ምርመራ ውጤቶቹ ቪዲዮዎችንም ያጋራል። ነገር ግን ስለ ሁሉም ነገር ግልጽ አይደለም።

"ስለ ጤና እና የአባላዘር በሽታዎች መዋሸት እንደማስፈለግ አስባለሁ። ግን ነገር መሰጠት የሌለባቸው ነገሮች አሉ፤ እነሱም የት እንደምሠራ፣ ምን እንደምሠራ ተቀባዮች እንዲከሱ የሚያደርጉ መረጃዎች ናቸው። ለምሳሌ ሙሉ ስም እና አድራሻ ሊሆን ይችላል።"

በዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) ውስጥ ፈቃድ ያላቸው ክሊኒኮች ቁጥጥር የሚደረግባቸው ሲሆን፤ ሰዎች ከሕጉ ጋር እንዲተዋወቁ የሚያስችል መረጃን በድረ ገጻቸው ላይ ያሰፍራሉ።

የዩኬ ተቆጣጣሪ ቢሮ በርካታ ቁጥር ያላቸው ቁጥጥር ያልተደረገባቸው የዘር ፍሬ ለጋሾችን ለፖሊስ እንደጠቆመ ተናግሯል።

"ቁጥጥር ያልተደረገበትን የዘር ፍሬ ከጋሽ መጠቀም ወንጀል አይደለም፤ እና ሕጉን እየጣሱ እንዳልሆነ ማወቅ አስፈላጊ ነው። ነገር ግን ለጋሾች ወይም የወንድ የዘር ፍሬን በማቅረብ ሂደት ውስጥ የተሳተፉ ሌሎች ሰዎች ከባድ ወንጀል እየፈጸሙ ሊሆን ይችላል" ብሏል።

በሕጉ መሠረት ለሰዎች ጥቅም ላይ እንዲውሉ "የሴት እንቁላል ወይም የወንድ የዘር ፍሬ መጠቀም፣ ማከማቸት፣ መግዛት፣ መመርመር፣ ማቀነባበር እና ማሠራጨት" ሕገ ወጥ ነው። እነዚህ ሁሉ ፈቃድ ባለው ክሊኒክ ካልተከናወኑ በስተቀር ሕገ ወጥ ናቸው።

የዩኬ ናይትድ የወሊድ (ፈርቲሊቲ) ተቆጣጣሪ ባልደረባ የሆኑት ክሌር ኢቲንግሀሰን ከሮበርት አልበን የቢቢሲ የምርመራ ቡድን በቀላሉ ያኘነው የዘር ፍሬ "አስደንጋጭ" እንደሆነ ተናግረዋል።

"ሕጉ ግልጽ ነው። ፈቃድ የሌለው አካል የወንድ የዘር ፍሬ ማዘጋጀት እና ማሠራጨት አይችልም። ይህንም ነው [አልበን] ያደረገው"።

አልበን በምላሹም ደንቦቹ በእሱ ላይ እንደማይተገበሩ ተናግሯል። ምክንያቱም የግል ልገሳዎችን መስጠት፣ ክፍያን ጨምሮ ሕጋዊ እንደሆነ ተናግሯል።

በተጨማሪም ለማንኛውም ተጋላጭ ለሆኑ ሴቶች "ቀጥተኛ አደጋ" እንዳልሆነ ተናግሯል።

ክሌር ኢቲንግሀሰን የፌስቡክ ባለቤት የሆነው ሜታ "ሕጉ እንዲጣስ እያመቻቸ ነው" በማለት በመጋቢት ወር በዩኬ ፓርላማ ኮሚቴ ላይ ተናግረዋል።

ድርጅታቸው ሜታን በቀጥታ ስለዚሁ ጉዳይ እንዳነጋገረው ቢገለጽም፤ ኃላፊዋ እንዲህ ዓይነቱ ድርጊቱ ከማኅበራዊ ትስስር ገፆች ወጣ ብሎ ይቀጥላል በማለት "ገሀዳዊ" እንደሆነች አክለው ገልጸዋል።

ተደጋጋሚ የጤና ማስጠንቀቂያዎች እና ድጋፍ የት ማግኘት እንደሚቻል እና ደኅንነቱ በተጠበቀ መንገድ ሕክምና ማግኘት እንደሚቻል አማራጮች መኖራቸው ችግሩን ሙሉ በሙሉ ባይፈታውም ጠቃሚ ይሆናል።"

በተጨማሪም ስለግል ደኅንነት ስጋቶችን አንስተዋል።

"ከለጋሾቹ መካከል በተፈጥሯዊ መፀነስ ብቸኛው ዘዴ አድርገው ያስተዋውቃሉ። ይህም በአንዳንድ ሁኔታዎች ሴቶች ወሲብ እንዲፈጽሙ ማስገደድ ነው።"

የፌስቡክ ባለቤት የሆነው ሜታ ቡድኖችን ወይም ልጥፎችን እንደሚገመግም እና ደንቦቹን "የሚጥሱ ይዘቶችን እንደሚያስወግድ" ተናግሯል።

"ተቆጣጣሪዎች እነዚህን መመሪያዎች የማይጥሱ፤ ነገር ግን ሕግ የሚጥሱ ይዘቶችን ለመጠቆም የተመደበ የሪፖርት አቀራረብ ሂደት አለን። በዚህ ጉዳይ ላይ ከሚመለከታቸው ባለሥልጣናት ጋር በቅርበት እየሠራን ነው" ሲል አክሏል።

የብሔራዊ የፖሊስ አዛዦች ምክር ቤት ቃል አቀባይ "ቁጥጥር ያልተደረገበት የወንድ የዘር ፍሬ ልገሳ ብዙ አደጋዎችን ያስከትላል እና ተጋላጭ የሆኑትን ሊበዘብዝ ይችላል። ማኅበረሰቡ አደጋዎችን እንዲገነዘብ እና ሕጋዊ መንገዶችን እንዲከተል በፅኑ እንመክራለን" ብሏል።