ትራምፕ በተገኙበት የዋይት ሐውስ ጋዜጠኞች የእራት ግብዣ ላይ ተኩስ ሲከፈት የተፈጠረውን ትርምስ የሚያሳይ ምስል

የዋይት ሐውስ ዘጋቢዎች የእራት ግብዣ ላይ የተገኙ እንግዶች ጠረጴዛ እና ወንበሮች ስር ተደብቀዋል

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, የዋይት ሐውስ ዘጋቢዎች የእራት ግብዣ ላይ የተገኙ እንግዶች ጠረጴዛ እና ወንበሮች ስር ተደብቀዋል
የንባብ ጊዜ: 3 ደቂቃ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በተገኙበት የዋይት ሐውስ ጋዜጠኞች የእራት ግብዣ ላይ ተኩስ ሲከፈት እርሳቸውን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት በፍጥነት አካባቢውን እንዲለቅቁ ተደርጓል።

የእራት ግብዣው ተዘጋጅቶ የነበረው በዋሺንግተን ዲሲ በሚገኘው የሒልተን ሆቴል ነው።

አንዳንድ የአሜሪካ ከፍተኛ ስም እና ዝና ያላቸው ፖለቲከኞች፣ ዲፕሎማቶች እና ጋዜጠኞች በዋሺንግተን ሒልተን አዳራሽ ውስጥ ተገኝተው ነበር።

ተኩሱ እንደተሰማ ከጠረጴዛ እና ወንበሮች ስር ለመደበቅ ተገድደዋል።

ተጠርጣሪው ነዋሪነቱን በካሊፎርኒያ ያደረገው የ31 ዓመቱ ኮል ቶማስ አለን መሆኑን የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ሰኞ ዕለት ፍርድ ቤት ቀርቦ ክስ እንደሚመሠረትበት ተገልጿል።

አንድ የአሜሪካ የደህንነት እና ጸጥታ ባልደረባ ጉዳት ደርሶበት በሆስፒታል ሕክምና እንደተደረገለት የአገሪቱ ባለሥልጣናት ተናግረዋል።

በምሽቱ የተፈጠረው በምስል ምን ይመስላል?

 የደህንነት እና ጸጥታ አባላት ትራምፕ ከመድረኩ ላይ በፍጥነት እንዲወርዱ ሲያደርጉ ሌሎች ወታደሮች ደግሞ አካባቢው ላይ ቅኝት አድርገዋል

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ, የደህንነት እና ጸጥታ አባላት ትራምፕ ከመድረኩ ላይ በፍጥነት እንዲወርዱ ሲያደርጉ ሌሎች ወታደሮች ደግሞ አካባቢው ላይ ቅኝት አድርገዋል
የደህንነት አባላት መሳሪያ ደቅነው

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የጤና ሚኒስትሩ ሮበርት ኤፍ ኬኔዲ ከአዳራሹ እንዲወጡ ሲደረግ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, የጤና ሚኒስትሩ ሮበርት ኤፍ ኬኔዲ ከአዳራሹ እንዲወጡ ሲደረግ
መሳሪያ የደገኑ የጸጥታ እና ደህንነት አባላት

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ከትራምፕ የቅርብ ረዳቶች መካከል አንዱ የሆኑት ስቴፈን ሚለር እና ባለቤታቸው ካቲ ደህንነቱ ወደተጠበቀበት ስፍራ ተወስደዋል

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ከትራምፕ የቅርብ ረዳቶች መካከል አንዱ የሆኑት ስቴፈን ሚለር እና ባለቤታቸው ካቲ ደህንነቱ ወደተጠበቀበት ስፍራ ተወስደዋል
የአሜሪካ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ማይክ ጆንሰን በደህንነት አባላት ከአዳራሹ እንዲወጡ ተደርጓል

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ, የአሜሪካ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ማይክ ጆንሰን በደህንነት አባላት ከአዳራሹ እንዲወጡ ተደርጓል
የሴት ጫማ እና ጌጥ

የፎቶው ባለመብት, Reuters

ተኩስ መክፈቱ የተጠረጠረውን ግለሰብ ምስል ትራምፕ አጋርተዋል

የፎቶው ባለመብት, @realDonaldTrump/ Truth Social

የምስሉ መግለጫ, በትራምፕ ትዕዛዝ ዋይት ሐውስ ያጋራው ምሰል ላይ ከላይ ምንም ዓይነት ልብስ ያልለበሰ ሰው እጆቹ የኋሊት ታስረው መሬት ላይ ተኝቶ ይታያል። ከጀርባው የደህንነት አባላት ቆመው ይታያሉ
ተኩስ በተከፈተበት ዋሺንግተን ሒልተን ሆቴል የፖሊስ መኪና ቆሞ ይታያል

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ, ተኩስ በተከፈተበት ዋሺንግተን ሒልተን ሆቴል የፖሊስ መኪና ቆሞ ይታያል
ትራምፕ የተጠርጣሪውን ምስል በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ካጋሩ በኋላ ብዙም ሳይቆይ፣ በዋይት ሐውስ ጋዜጣዊ መስጫ ክፍል ውስጥ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቆወች ምላሽ ሰጥተዋል

የፎቶው ባለመብት, Anadolu via Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ትራምፕ የተጠርጣሪውን ምስል በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ካጋሩ በኋላ ብዙም ሳይቆይ፣ በዋይት ሐውስ ጋዜጣዊ መስጫ ክፍል ውስጥ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቆወች ምላሽ ሰጥተዋል
 በርካቶቹ የዋይት ሐውስ ዘጋቢዎች በግብዣው ላይ ለመገኘት ያደረጉትን እራት ልብስ እና ሱፍ እንደለበሱ የትራምፕን ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተገኝተዋል

የፎቶው ባለመብት, AFP via Getty Images

የምስሉ መግለጫ, በርካቶቹ የዋይት ሐውስ ዘጋቢዎች በግብዣው ላይ ለመገኘት ያደረጉትን እራት ልብስ እና ሱፍ እንደለበሱ የትራምፕን ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተገኝተዋል
ሜላኒያ ትራምፕ ከካሮላይን ሌይቪት፣ ፒት ሄግሴት እና ማርኮ ሩቢዮ አጠገብ ቆማለች

የፎቶው ባለመብት, Bloomberg via Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ሜላኒያ ትራምፕ ከካሮላይን ሌይቪት፣ ፒት ሄግሴት፣ ማርኮ ሩቢዮ እና ሌሎች ባለሥልታነት አጠገብ ቆማ ትታያለች። ትራምፕ ለባለቤታቸው ሜላኒያ የሒልተን ሆቴሉ ክስተት "አሰቃቂ" እንደነበር ተናግረዋል
እንግዶች አዳራሹን ለቅቀው ከወጡ በኋላ የእራት ግብዣው ይቀጥላል ተብሎ የነበረ በመሆኑ ግራ በመጋባት ደጅ ቆመው ታይተዋል

የፎቶው ባለመብት, EPA

የምስሉ መግለጫ, እንግዶች አዳራሹን ለቅቀው ከወጡ በኋላ የእራት ግብዣው ይቀጥላል ተብሎ የነበረ በመሆኑ ግራ በመጋባት ደጅ ቆመው ታይተዋል