ሊቨርፑል ከቼልሲ እና ዌስት ሃም ከአርሰናል፡ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ግምቶች

የንባብ ጊዜ: 3 ደቂቃ

አርሰናል ቀሪ ሦስት ጨዋታዎችን ካሸነፈ የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን መሆኑን ያረጋግጣል።

መድፈኞቹ ይህንን ለማሳካት በወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኘውን ዌስት ሃምን በማሸነፍ ጉዞውን ይጀምራሉ።

"የአርሰናል ደጋፊዎች ይህን መሰሉን ጨዋታ በማሸነፍ ፈተናውን አልፈው ዋንጫውን እንደሚያሳኩ ይገምታሉ" ሲል የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱተን ገልጿል።

ሱተን ይህንን ጨምሮ የ36ኛ ሳምንት እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን እንደሚከተለው ገምቷል።

ቅዳሜ

ሊቨርፑል ከ ቼልሲ

በውድድር ዓመቱ መጥፎ ምሽትን ባሳለፉበት የማንቸስተር ዩናይትድ ጨዋታ ቢሸነፉም ሊቨርፑሎች በሻምፒዮንስ ሊግ የሚያሳትፋቸውን ደረጃ ይዘው እንደሚያጠናቅቁ እገምታለሁ።

ቼልሲ የበለጠ ችግር ውስጥ ሲሆን፣ በስድስት ተከታታይ የሊግ ጨዋታዎችም ተሸንፏል።

ከዚህ ጨዋታም ውጤት ያገኛሉ ብዬ አልጠብቅም።

ግምት፡ 2 - 1

ብራይተን ከ ዎልቭስ

ብራይተን ባለፈው ሳምንት በኒውካስል ቢሸነፍም ይህንን ጨዋታ እንደሚያሸንፍ እገምታለሁ።

ዎልቭስ አቋሙን እያሻሻለ ቢመጣም ወደ ውጤት መቀየር እና ማስቀጠል አልቻለም።

ግምት፡ 2 - 0

ፉልሃም ከ በርንመዝ

ዘንድሮ የፉልሃምን ጨዋታ ለመገመት አስቸጋሪ ሆኖብኛል።

ቡድኑ ጥሩ ጊዜ እያሳለፈ ቢሆንም በርንመዝ ላለፉት 15 ጨዋታዎች ሽንፈትን አላስተናገደም።

በመጀመሪያው ዙር ያሸነፉት በርንመዞች በዚህ ጨዋታም እንደሚያሸንፉ እገመታለሁ።

ግምት፡ 1 - 2

ሰንደርላንድ ከ ማንቸስተር ዩናይትድ

ማንቸስተር ዩናይትድ ባለፈው ሳምንት ሊቨርፑልን አሸንፎ የሻምፒዮንስ ሊግ ተሳታፊነቱን አረጋግጧል።

ቡድኑ በአሠልጣኝ ማይክል ካሪክ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ዙሪያ በቅርቡ ውሳኔ መስጠት ይኖርበታል።

ሰንደርላንድ በሜዳው በኖቲንግሃም ፎረስት 5 ለምንም ቢሸነፍም በሜዳው ጠንካራ መሆኑን ደጋግሞ አሳይቷል።

ከዚህ ጨዋታም አንድ ነጥብ እንደሚያገኙ እገምታለሁ።

ግምት፡ 1 - 1

ማንቸስተር ሲቲ ከ ብሬንትፎርድ

ሲቲ ባለፈው ሳምንት ከኤቨርተን ጋር ሦስት አቻ መለያየቱን ተከትሎ የዋንጫው መዳረሻን የመወሰን አቅሙን አጥቷል።

ሲቲ ይህንን ጨዋታ ለማሸነፍ ጎሎችን ማስቆጠር ይኖርበታል።

ብሬንትፎርድ በመጀመሪያው ዙር ለጥቂት ነበር በሲቲ የተሸነፈው።

በዚህ ጨዋታ ኧርሊንግ ሃላንድ ጎል አስቆጥሮ ሲቲ እንደሚያሸንፍ እገምታለሁ።

ግምት፡ 3 - 1

እሑድ

በርንሌይ ከ አስቶን ቪላ

አምስተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው ቪላ በወራጅ ቀጣና ውስጥ በነበረው ቶተንሃም በመሸነፉ ደጋፊዎቹ ቁጣቸውን ገልጸዋል።

አሠልጣኝ ኡናይ ኤምሬ በዩሮፓ ሊግ ከፎረስት ጋር ለነበረባቸው ጨዋታ በርካታ ተጫዋቾችን ቀይረው አሰልፈው ነበር።

ቡድኑ ደካማ ቢሆንም እንኳን አሠልጣኝ የሌለውን በርንሌይን እንደሚያሸንፍ እገምታለሁ።

ግምት፡ 0 - 2

ክሪስታል ፓላስ ከ ኤቨርተን

ፓላስም የአውሮፓ መድረክ ተሳትፎው በሊጉ ጨዋታ ላይ ያለውን ትኩረት የቀነሰው ሌላኛው ቡድን ነው።

ኤቨርተን በበኩሉ ባለቀ ሰዓት ግቦችን የማስተናገድ አባዜ እንዳለበት ከሊቨርፑል፣ ከዌስት ሃም እና ከማንቸስተር ሲቲ ጋር አሳይቷል።

አሠልጣኝ ዴቪድ ሞዬስ በዚህ ጨዋታ ግን የተለየ ውጤት እንደሚያስመዘግቡ አስባለሁ።

ግምት፡ 0 - 1

ኖቲንግሃም ፎረስት ከ ኒውካስል ዩናይትድ

ፎረስት እስካሁን ከመውረድ መትረፉን አላረጋገጠም።

ቡድኑ በአሠልጣኝ ቪቶር ፔሬራ ስር ወደ ጥሩ አቋም መመለስ ቢችልም ባለፈው ሳምንት ሞርጋን ጊብስ ተጎድቶ መውጣቱ ቡድኑን ያሳሳዋል።

ከቪላ ጋር በዩሮፓ ሊግ የደረሰባቸው ሽንፈት የሚያስከትለው ተጽእኖውም የሚታይ ነው።

ኒውካስል ባለፈው ሳምንት ብራይተንን ቢያሸንፍም ቡድኑ አሳማኝ ባለመሆኑ ይህ ጨዋታ በአቻ ውጤት ይጠናቀቃል።

ግምት፡ 1 - 1

ዌስት ሃም ከ አርሰናል

ቡካዮ ሳካ መመለሱን ተከትሎ የአርሰናል የፊት መስመር የተለየ መልክ ይዟል።

በወራጅ ቀጣና ውስጥ ለሚገኘው ዌስት ሃም ይህንን ጨዋታ ማሸነፍ ከባድ ይሆንበታል።

ከዚህ ጨዋታ አንድ ነጥብ ማግኘት ለዌስት ሃም መጥፎ የሚባል ውጤት አይደለም።

አርሰናል ላለፉት ሁለት ዓመታት በለንደን ስታዲየም ድል ያስመዘገበ ሲሆን፣ በዚህ ጨዋታም ነጥብ ይጥላል ብዬ አልገምትም።

ግምት፡ 1 - 3

ሰኞ

ቶተንሃም ከ ሊድስ ዩናይትድ

ሊድስ ከሊጉ እንደማይወርድ ማረጋገጡ ለስፐርስ ይጠቅመዋል።

ስፐርስ ባለፈው ሳምንት በጥሩ እንቅስቃሴ ቪላን አሸንፎ መውጣት ችሏል።

በዚህ ጨዋታም ተመሳሳይ ነገር የምጠብቅ ስሆን ውጤቱም ከመጀመሪያው ዙር ጋር ተመሳሳይ እንደሚሆን እገምታለሁ።

ግምት፡ 2 - 1