ኢላን መስክ ስፔስኤክስ ላይ በደረሰ ዓለም አቀፋዊ የገበያ ውድቀት ምክንያት የትሪሊየነርነት ማዕረጉን አጣ

ታትሟል
የንባብ ጊዜ: 2 ደቂቃ

የቴክኖሎጂ ፈጣሪው ኢላን መስክ በኩባንያው ስፔስኤክስ የአክሲዮን ሽያጭ የመጀመሪያው የዓለማችን ትሪሊየነር ከሆነ ከሁለት ሳምንት በኋላ ይህን ማዕረጉን አጣ።

በየቀኑ የሚወጣው የብሉምበርግ የቢሊየነሮች ዝርዝር መረጃ ማክሰኞ ዕለት የመስክን ሀብት ከ14 ቀን በፊት ከነበረበት 1.11 ትሪሊየን ዶላር ወደ 957 ቢሊዮን ዶላር ዝቅ አድርጎ ገምቶታል።

ሀብቱ ወደ ኋላ የተመለሰው የስፔስኤክስ እና ቴስላ የአክሲዮን ድርሻ ሰፊ ውድቀት ካሳየ በኋላ ነው። የአክሲዮን ድርሻው መውረዱ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤአይ) ዘላቂ የሆነ ትርፍ ማግኘት ላይ እያደገ በመጣው ጥርጣሪ የተገፋፋ ነው።

ምንም እንኳ መስክ ሀብቱ ቢቀንስም አሁንም የዓለማችን አንደኛ ከበርቴ ነው። ሀብቱ በቅርብ የሚከተሉትን ጥሎ የሄደ ነው።

ቢሊየነሩ ባለፈው ሰኔ 5/2018 ዓ.ም. ሲጠበቅ የነበረው የኅዋ ኩባንያው ስፔስኤክስ በናስዳቅ መገበያያ ድርሻዎቹ መሸጣቸውን ተክሎ ታሪክ ሰርቷል።

በመጀመሪያ ለሕዝብ የቀረበው የአንድ አክሲዮን ድርሻ 135 ዶላር የነበረ ሲሆን ሽያጩ ሲከፈት ግን 150 ዶላር ገብቷል።

የአክሲዮን ሽያጩ የሮኬት እና የሳተላይት አምራቹን ኩባንያው 1.77 ትሪሊዮን ዶላር ዋጋ እንዲገመት አስችሏል። መስክ የስፔስኤክስ 42 በመቶ ድርሻ ባለቤት በመሆኑ የአክሲዮን ሽያጩ የአንድ ትሪሊዮን ዶላር የወረቀት ሀብት ባለቤት አድርጎታል።

ገበያ ላይ በወጣ በሳምንቱ የመዋዕለ ነዋይ አፍሳሾች ብርቱ ፍላጎት የስፔስኤክስ የአንድ አክሲዮን ድርሻ 225.64 ዶላር አድርሷል። ይህም የመስክን ሀብት ወደ 1.32 ትሪሊዮን ዶላር ሰቅሎታል።

ይሁን እንጂ ገበያው ረጅም ጊዜ መቆየት አልቻለም።

በመደበኛ ወጪዎች፣ የሠው ሰራሽ አስተውሎት የመሠረተ ልማት ዋጋ እና የወለድ ምጣኔ ሰፊ የቴክኖሎጂ ሽያጭ ውድቀትን አስከትሏል። በተለይ እንደ ነቪዳ፣ ኢንቴል እና ኤኤምዲ ያሉ የዓለማችን የቴክኖሎጅ ግዡፍ ኩባንያዎች ክፉኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ይሁን እንጂ ስፔስኤክስ የዚህ ለውጥ ከባዱ ዱላ አርፎበታል። የአክሲዮን ድርሻው በ30 በመቶ በማሽቆልቆል አንድ ድርሻ 156 ዶላር ገብቷል።

ሰኞ ብቻ በነበረው ገበያ በአንድ ቀን 16 በመቶ በመቀነስ 240 ቢሊዮን ዶላር የተገመተ የመስክ የግል ሀበት እጥቷል።

በተመሳሳይ ሁኔታ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ አምራች የሆነው ኩባንያው ቴስላ በቀን በስድስት በመቶ ድርሻው በመቀነሱ ጉዳቱን አባብሶታል። መስክ ለሽያጭ የቀረበው 12 በመቶ የቴስላ ድርሻ ባለቤት ነው።

የመስክ የትሪሊየነርነት ማዕረግ በሀብቱ ክምችት ምክንያት በተለየ የተጋለጠ ነው። በተለመደው አካሄድ ቢሊየነሮች የሀብት ምርጫቸው ሰፊ ሲሆን፤ የመስክ ሀብት ግን ሁለቱ ኩባንያዎች ላይ የተንጠለጠለ ነው። 80 በመቶ የሀብቱን ድርሻ በያዘው ስፔስክኤክስ እና ቴስላ ላይ የተንጠለጠለ ነው።