ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
በምርጫ ተሸንፈው ፓስፖርታቸው የተሰረዘው ቦልሶናሮ ከብራዚል ሸሽተው አሜሪካ መግባታቸውን አስተባበሉ
የብራዚል የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባል ፍላቪዮ ቦልሶናሮ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ መሸነፋቸውን ተከትሎ ሚያሚ፣ አሜሪካ ገብተው "አገሬን ለመልቀቅ ፍላጎት አልነበረኝም" ብለዋል።
"ብራዚልን ሸሽቼ አልወጣሁም፤ ለብራዚል ስል ነው የወጣሁት" ሲሉ ለቅቀው ከወጡ በኋላ ባወጡት መግለጫ ተናግረዋል።
በተከፈተባቸው የወንጀል ምርመራ ምክንያት ፓስፖርታቸው ከተሰረዘ በኋላ አሜሪካ ለእርሳቸው እና ለቤተሰባቸው ቪዛ ሰጥታለች። ቦልሶናሮ ምንም ወንጀል እንዳልሠሩ ይናገራሉ።
ረቡዕ ዕለት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለጋዜጠኞች "እዚህ አገር ለመግባት ፈቃድ ሰጥተናቸዋል" ብለዋል።
አዲስ የተመረጡት ፕሬዝዳንት ሉዊስ ኢንሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ፣ ቦልሶናሮ በድብቅ አገሪቱን ለቅቀው መውጣታቸውን ተችተዋል።
"የሚደብቁት ነገር ከሌላቸው ምንም የሚያስፈራቸው ነገር የለም" ብለዋል።
የቦልሶናሮ ፍሎሪዳ መግባት ለቀናት ያሉበት ላልታወቀው ፕሬዝዳንታዊ እጩ ግርታን ያጠራ ሆኗል። አርጀንቲና መጓዛቸው ከተዘገበ በኋላ ማክሰኞ ዕለት አሜሪካ መግባታቸው ተነግሯል።
ቦልሶናሮ ባወጡት መግለጫ የአርጀንቲና እና የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶችን እንዲሁም "እንደ አገሬ ሕዝቦች ተመሳሳይ እሴቶችን የሚጋሩ" ያሏቸውን የአሜሪካን ሕዝብ አመስግነዋል።
"አገሬን ለቅቄ የመውጣት ሀሳብ አልነበረኝም፤ ይሁን እንጂ ነገሩ ወዴት እያመራ እንደሆነ በደንብ አውቃለሁ" ብለዋል።
"ከሚለያይ አገዛዝ የአገሬ ሕዝብ የሚገባውን መሪ ለመሆን ነው የወጣሁት" ብለዋል።
ራሳቸውን የመፈንቅለ መንግሥት ተጎጂ እና የፖለቲካ ተሳዳጅ አድርገው ያቀረት ቦልሶናሮ ወደ አሜሪካ የተጓዙት ቤተሰባቸውን ለመጠቅ መሆኑን ተናግረዋል።
ቦልሶናሮ በረዥም መግለጫቸው በማስረጃ ያልተደረገፈ "የምርጫ ማጭበርበር" መፈፀሙን ተናግረዋል።
ረቡዕ ዕለት በቦልሶናሮ መግለጫ ላይ ስለተጠቀሰው ክስ ትራምፕ ተጠይቀው ለማውራት ፈቃደኛ አልሆኑም።
ቦልሶናሮ የመጀመሪያውን ዙር የብራዚል ምርጫ ካሸነፉ በኋላ፤ ፕሬዝዳንት ሉላ ሁለተኛውን ዙር በአራት ሚሊዮን ድምፆች ብልጫ አሸንፈዋል። ይህም ከመራጮች ቁጥር መጨመር እና ካልወሰኑ መራጮች ጋር ተያይዟል።
የምርጫው ውጤት በፍላቪዮ አባት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዣይር ቦልሶናሮ በተሰየመው የብራዚል ከፍተኛ የምርጫ ፍርድ ቤት ተረጋግጧል።
ቦልሶናሮ የገቡበት መነጋገሪያ የሆነው የአርጀንቲና የዜና ድረ ገፅ የምክር ቤት አባሉ በአርጀንቲና እና ብራዚል ድንበር አቋርጠው ከገቡ በሏላ ወደ አሜሪካ ጉዟቸውን ጀምረዋል የሚል ዘገባ ካወጣ በኋላ ነው።
ይህን ጭምጭምታ የብራዚል ፖሊስ የመረመረ ሲሆን ቦልሶናሮ አገሪቱን ለቅቀው ስለመውጣታቸው ምንም ማስረጃ አላገኘም። የአርጀንቲና ባለሥልጣናትም ድንበሩን ስለመሻገራቸው መረጃ እንደሌላቸው ተናግረዋል።
ለአጭር ጊዜም ቢሆን ቦልሶናሮ በምርጫ በመሸነፋቸው እና በተከፈተባቸው የወንጀል ምርመራ ፓስፖርታቸውን በመነጠቃቸው ተደብቀው ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል።
ይሁን እንጂ በተሰጣቸው ቀነ ገደብ ፓስፖርታቸውን ማስረከብ ባለመቻላቸው፤ የብራዚል ባለሥልጣናት ሰነዳቸው እንዲሰረዝ እና ፖሊስ የድንበር ጣቢያዎችን እንዲፈትሽ ትዕዛዝ ሰጥተዋል።
ወዲያው ቦልሶናሮ አገሪቱን ለቅቀው መውጣታቸው የተወራ ሲሆን፤ ጠበቃቸውም የት እንዳሉ እንደማያውቁ ተናግረዋል።
ከሰዓታት በኋላ በርካታ የቢቢሲ ምንጮች ወደ አሜሪካ እየተጓዙ እንደሆነ ተናግረዋል።