የጥምቀት አከባበር በምሥል

የከተራ በዓል በባቱ
ታትሟል
የንባብ ጊዜ: 3 ደቂቃ

በመላው ኢትዮጵያ የክርስትና እምነት ተከታዮች የኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት በዓልን እያከበሩ ነው።

የጥምቀት በዓል ከዋዜማው ጥር 10 ጀምሮ ጥር 11 የሚከበር ሲሆን ጥር 12 ደግሞ የቃና ዘገሊላ በዓል እንዲሁ በድምቀት ይከበራል።

ከጥምቀት በዓል ዕለት ቀደም ብሎ ባለው ቀን በሚከበረው የከተራ በዓል፤ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስቲያናት ታቦታት ወጥተው የጥምቀት በዓል ወደሚከበርባቸው ቦታ በሕዝብ ታጅበው ይጓዛሉ።

አዲስ አበባ የሚገኘው ጃን ሜዳ እና ጎንደር ጥምቀት በተለየ ሁኔታ የሚከበርባቸው ሥፍራዎች መካከል ሲሆኑ፤ ከምዕመናን በተጨማሪ የተለያዩ አገራት ቱሪስቶች በዓሉን ለመታደም ይመጣሉ።

ከተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች የዛሬውን የበዓሉ አከባበር የሚያሳዩ ምሥሎችን እንዲህ አጠናቅረናል።

የጎንደር ከተማ ጥምቀት አከባበር
የምስሉ መግለጫ, የጥምቀት በዓል በድምቀት ከሚከበርባቸው የአገሪቱ ከተሞች አንዷ ጎንደር ነች
በአዲስ አበባ ከተማ በአበበ ቢቂላ ስቴዲየም አካባቢ የነበረው ሥነ ሥርዓት
የምስሉ መግለጫ, በአዲስ አበባ ከተማ በአበበ ቢቂላ ስቴዲየም አካባቢ የነበረው ሥነ ሥርዓት
በአዲስ አበባ ከተማ በአበበ ቢቂላ ስቴዲየም አካባቢ የነበረው የፀበል መረጨት ሥነ ሥርዓት
የምስሉ መግለጫ, በአዲስ አበባ ከተማ በአበበ ቢቂላ ስቴዲየም አካባቢ የነበረው የፀበል መረጨት ሥነ ሥርዓት
በኦሮሚያ ክልል ባቱ ከተማ ትናንት በከተራ ዕለት ታቦታት በዳምባል ሐይቅ በመጓዝ ወደ ማደሪያቸው አምርተዋል
የምስሉ መግለጫ, በኦሮሚያ ክልል ባቱ ከተማ ትናንት በከተራ ዕለት ታቦታት በዳምባል ሐይቅ በመጓዝ ወደ ማደሪያቸው አምርተዋል
ሐረር ከተማ ጥምቀት
የምስሉ መግለጫ, በሐረር ከተማ ትናንት ከየደብሩ የወጡ ታቦታት እየተመለሱ እንደሆነ የሐረሪ ክልል ፖሊስ ገልጿል
ዛሬ ጠዋት በአዲስ አበባ ከተማ ጃን ሜዳ የነበረው የጥምቀት በዓል አከባባር
የምስሉ መግለጫ, የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በፌስቡክ ገጻቸው ካጋሯቸው የጥምቀት በዓል ምሥሎች አንዱ ይሄ ነው
በጎንደር ከተማ የጥምቀት ምስሎች ላይ በዓሉን የታደሙ የውጭ አገር ዜጎች ይታያሉ
የምስሉ መግለጫ, በጎንደር ከተማ የጥምቀት ምሥሎች ላይ በዓሉን የታደሙ የውጭ አገር ዜጎች ይታያሉ
መቀለ ከተማ
የምስሉ መግለጫ, ትግራይ ክልል መቀለ ከተማ የነበረው የጥምቀት አከባበር
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ምዕመናን የጥምቀት በዓልን በተለያዩ መንፈሳዊ ሥነሥርዓቶች ማክበራቸውን ኢቢሲ ዘግቧል
የምስሉ መግለጫ, የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ምዕመናን የጥምቀት በዓልን በተለያዩ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓቶች አክብረዋል
በአዲስ አበባ ከተማ አበበ ቢቂላ ስቴዲየም አካባቢ የነበረው ፀበል መረጨት ሥነ ሥርዓት
የምስሉ መግለጫ, በአዲስ አበባ ከተማ አበበ ቢቂላ ስቴዲየም አካባቢ የነበረው ፀበል መረጨት ሥነ ሥርዓት
በአዲስ አበባ ከተማ ጃን ሜዳ የጸበል መርጨት ሥነ ሥርዓት
የምስሉ መግለጫ, በአዲስ አበባ ከተማ ጃን ሜዳ የፀበል መርጨት ሥነ ሥርዓት
አርባ ምንጭ
የምስሉ መግለጫ, በአርባ ምንጭ ከተማ አምስት አድባሮች በሚያድሩበት ፈለገ ዮርዳኖስ የመስቀል ደመራ እና የጥምቀት ሥርዓት ማክበሪያ ቦታ በዓሉ በድምቀት እየተከበረ መሆኑን የከተማዋ ኮሚዩኒኬሽን ገልጿል
የካቶሊክ ቄሶች
የምስሉ መግለጫ, በአዲስ አበባ በአበበ ቢቂላ ስቴዲየም አካባቢ በነበረው የባሕረ ጥምቀት ሥነ ሥርዓት ላይ የካቶሊክ አባቶች ተገኝተዋል
አዲስ አበባ
የምስሉ መግለጫ, አዲስ አበባ ከተማ
በባቱ ከተማ ታቦታት ወደ ማደሪያቸው የሚሄዱት ሐይቅ ተሻግረው ነው
የምስሉ መግለጫ, በባቱ ከተማ ታቦታት ወደ ማደሪያቸው የሚሄዱት ሐይቅ ተሻግረው ነው
አሶሳ ከተማ አከባበር
የምስሉ መግለጫ, በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዋና ከተማ አሶሳ የጥምቀት በዓል አከባበር
የባቱ ከተማ
የምስሉ መግለጫ, የባቱ ከተማ የጥምቀት አከባበር
የአዲስ አበባ ከተማ ጥምቀት በዓል አከባበር
የምስሉ መግለጫ, በአዲስ አበባ ከተማ ጥምቀት በዓል አከባበር