ትራምፕ የሰው ሠራሽ አስተውሎት አደጋ እየሆነ ይመጣል መባሉን ተፎካካሪያቸውን ቻይናን በመጥቀስ አጣጣሉ

ትራምፕ

የፎቶው ባለመብት, EPA

ታትሟል
የንባብ ጊዜ: 2 ደቂቃ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባለሙያዎች በሰው ሠራሽ አስተውሎት የተነሳ ሊፈጠሩ የሚችሉ አደጋዎችን በሚመለከት ለቀናት ከባድ ማስጠንቀቂያ ከሰጡ በኋላ ይፈጠራሉ የተባሉ ስጋቶችን አጣጣሉ።

ትራምፕ አየርላንድን በጎበኙበት ወቅት "እጅግ አሉታዊ የሆኑ ሐሳቦችን የሚያሰራጩ ብዙ ሰዎች ወይም ቡድኖች አሉ። እነሱ መነሳት የማይገባቸውን ጉዳዮች እያነሱ እንዲሁም በእርግጥ የማይከሰቱ ነገሮችን እያወሩ ነው" ብለዋል።

ቀድሞ የአንትሮፒክ ተመራማሪ ከሰጡት ማስጠንቀቂያዎች መካከል "አሁን ያለው የእድገት ፍጥነት ከቀጠለ ሁላችንም በቅርብ ጊዜ ውስጥ የመሞት እድላችን ከፍተኛ ነው" የሚለው ይገኝበታል።

ቅዳሜ ዕለት፣ ከፍተኛ የኢንዱስትሪ ኃላፊዎች በጋራ በመሆን የሰው ሠራሽ አስተውሎት ፍጥነቱ እንዲቀንስ ጥሪ አቅርበዋል።

ትራምፕ ሀሳቡን በቀጥታ ባያነሱትም "ቻይናን በሰው ሠራሽ አስተውሎት እየመራን ነው… እና እውነቱን ለመናገር፣ ሰው ሠራሽን የሚያሸንፍ ሁሉን ስለሚያሸንፍ በዚህ መንገድ መቀጠል እፈልጋለሁ" ብለዋል።

ትራምፕ ከጥቂት ቀናት በፊት አንትሮፒክን የለቀቁት የሰው ሠራሽ አስተውሎት ተመራማሪ ጃኮብ ኮክሰን ማስጠንቀቂያውን በሰጡበት ቀን ለቢቢሲ እንደተናገሩት ሥርዓቱን የሚያዘጋጁ ባለሙያዎች ለሰው ልጅ የወደፊት ዕጣ ፈንታ "በእውነት ፈርተዋል" ብለዋል።

ለኦፕን ኤአይ ይሰሩ የነበሩት ኮክሰን ፍጥነቱን እንዲቀንስ በቀረበው ምክረ ሃሳብ ላይ ተስማምተው ነገር ግን ከቻይና ጋር መተባበር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

ቅዳሜ ዕለት የኤክስኤአይ ባለቤት የሆነው ኤለን መስክ እንዲሁም የኦፕን ኤአዩ ሳም አልትማን በአንትሮፒክ ሥራ አስፈጻሚ ዳሪዮ አሞዴይ የተሰጠውን ማስጠንቀቂያ ደግፈዋል።

Skip podcast promotion and continue reading
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናል

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት

ይህንን በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

End of podcast promotion

ኃላፊው የሰው ሠራሽ አስተውሎት "የሆነ ነገርን ፈጽሞ የማበላሸቱን ዕድሉን ለመቀነስ" ፍጥነቱን መቀነስ አለበት ብለው ነበር።

የአንትሮፒክ ኃላፊ "ማንኛውም ማዘግየት ቻይና ቀድማ እንዳትሄድ መገደብ አለበት" ብለዋል።

በኤአይ ዙሪያ የሚነሱ ሃሳቦች ከባድ ክርክር በማስነሳት ለብዙ የዓለም መሪዎች ፈታኝ ሁኔታን ደቅነዋል።

በአንድ በኩል፣ ዘርፉ የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማሳደግ ትልቅ ዕድል እና ጊዜ ያለፈባቸውን ዲጂታል ሥርዓቶች እና የሥራ መንገዶችን ለማሻሻል እንደ መንገድ ይታያል።

በሌላ በኩል ደግሞ ኤአይ በጣም የተሳሳተባቸው የሚመስሉ በርካታ ክስተቶችም አጋጥመዋል።

ኦፕንኤአይ በነሐሴ ወር ላይ ደህንነትን ለማሻሻል በጣም የላቁ የኤአይ ሞዴሎቹን ማሰልጠኑን እንዳዘገየ ተናግሯል።

የቻትጂፒቲ አምራች ኩባንያ የኤአይ ወኪሎቹ የተቀመጡ የደህንነት መከላከያዎች አልፈው ሁጊንግ ፌስን ከጠለፉ በኋላ አዳዲስ እርምጃዎችን እያከለ መሆኑን ተናግሯል።

በዚያው ወር በዓለም ላይ ካሉት እጅግ ከፍተኛ አቅም ያላቸው የኤአይ መሳሪያዎች መካከል ሁለቱን ሰዎች በሳይበር ጥቃቶች ለማታለል ሐሰተኛ የሰው ልጅ መገለጫዎችን እንደፈጠሩ ይፋ ተደርጓል።

የእንግሊዝ የኤአይ ደህንነት ተቋም የአንትሮፒክ ሚቶስ አይአይ የግል መልዕክቶችን በመላክ፣ እውነተኛ ሰዎችን በመምሰል ሐሰተኛ አካውንቶችን በማዘጋጀት እና ከዚያም ማስረጃውን በመደበቅ አገልግሎቶችን ለማግኘት መሞከሩን አስታውቋል።

የትራምፕ አስተዳደር አሜሪካ በብሔራዊ ደህንነት ጉዳይ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ የበላይነትን ማስጠበቅ እንዳለባት ቢከራከርም፣ በቴክኖሎጂው ምክንያት ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን በተመለከተ ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አምኗል።

በሳምንቱ መጨረሻ በዋና ዋና የሰው ሠራሽ አስተውሎት ኩባንያዎች ኃላፊዎች የቀረበው ጥሪ በዋሽንግተን ውይይት አስነስቷል።

በዚህ ወቅት ሕግ አውጪዎች ፈጣን የኤአይ እድገትን በተመለከተ ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን ለመፍታት ጫና እየገጠማቸው ነው።

እሁድ እለት፣ የሪፐብሊካን ፓርቲ ከፍተኛ የምክር ቤት አፈ ጉባኤ ማይክ ጆንሰን፣ ለሲኤንኤን በሰጡት ቃለ ምልልስ ኤአይ ላይ የሚደረገው ቁጥጥር በፍጥነት እንዲደረግ የሚለው በጥንቃቄ መታየት አንዳለበት አሳስበዋል። ለዚህም በምክንያትነት ያነሱት "የአሜሪካን ፈጠራ ሊያደናቅፍ ይችላል" የሚል ነው።