ማንቸስተር ሲቲ ከቼልሲ፡ የኤፍ ኤ ካፕ የፍጻሜ እና የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ግምት

ማንቸስተር ሲቲ ከቼልሲ
ታትሟል
የንባብ ጊዜ: 3 ደቂቃ

145ኛው የኤፍ ኤ ካፕ የፍጻሜ ጨዋታ ቅዳሜ ዕለት በማንቸስተር ሲቲ እና በቼልሲ መካከል ዌምብሌይ ላይ ይከናወናል።

ቼልሲ ባለፉት 13 ጨዋታዎች ማንቸስተር ሲቲን አሸንፎ አያውቅም።

በ2021 የሻምፒዮንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ ሁለቱ ቡድኖች ተገናኝተው ካይ ሃቨርትዝ ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ የለንደኑ ክለብ አሸናፊ በመሆን የፔፕ ጋርዲዮላን ቡድን ዋንጫ ቀምቷል።

የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱተን የኤፍ ኤ ካፕን የፍጻሜ ጨዋታን ጨምሮ የፕሪሚየር ሊጉን ጨዋታዎች እንደሚከተለው ገምቷል።

አርብ

አስቶን ቪላ ከ ሊቨርፑል

ቪላ በዩሮፓ ሊግ ላለበት የፍጻሜ ጨዋታ ተጫዋቾችን ቀይሮ ከቶተንሃመን ሆትስፐር ጋር ባደረገው ጨዋታ ተሸንፏል።

ቡድኑ ለፍጻሜው ይረዳው ዘንድ በዚህ ጨዋታ በሙሉ አቋሙ መጫወት ይጠበቅበታል።

ሊቨርፑል ወጥ አቋም ማሳየት ካለመቻሉም በላይ እስከ አምስት ያለውን ደረጃ ይዞ የማጠናቀቁ ጉዳይ አልተረጋገጠም።

ግምት፡ 1 - 1

ቅዳሜ

ቼልሲ ከ ማንቸስተር ሲቲ (የኤፍ ኤ ካፕ የፍጻሜ ጨዋታ)

ፔፕ አጥቂው ኧርሊንግ ሃላንድን ጨምሮ በርካታ ተጫዋቾችን በማሳረፍ በሳምንቱ አጋማሽ ክሪስታል ፓላስን አሸንፈዋል።

የሚመለሱት ተጫዋቾች ከተሰጣቸው እረፍት ተጠቃሚ ይሆናሉ።

ቼልሲ ደካማ አቋም እያሳየ የቀጠለ ሲሆን በዚህ ጨዋታ ጥሩ መንቀሳቀስ ካልቻለ መጥፎ ውጤት ያስመዘግባል።

ግምት፡ 0 - 5

እሑድ

ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ኖቲንግሃም ፎረስት

ማንቸስተር ዩናይትድ ከኖቲንግሃም ፎረስት

ፎረስት በሊጉ መቆየቱን ዩናይትድም በሻምፒዮንስ ሊግ መሳተፉን በማረጋገጡ ብዙም ትኩረት የሚስብ ጨዋታ አይሆንም።

ጨዋታውን ለመገመት ከባድ ቢሆንም የዩናይትዱ አስልጣኝ ማይክል ካሪክ በጥሩ ውጤት የሜዳውን ጨዋታ ለማጠናቀቅ ወደ ሜዳ እንደሚገባ ይገመታል።

ግምት፡ 2 - 0

ብሬንትፎርድ ከ ክሪስታል ፓላስ

ፓላስ ትኩረት ያደረገው በዩሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ ላይ ነው።

ብሬንትፎርድ በቡኩሉ በአውሮፓ መድረክ ለመሳተፍ ጨዋታውን ለማሸነፍ ወደ ሜዳ ይገባል።

በዚህ ምክንያት ጨዋታውን ብሬንትፎርድ እንደሚያሽንፍ እገምታለሁ።

ግምት፡ 1 - 0

ኤቨርተን ከ ሰንደርላንድ

ሁለቱም በደረጃ ሰንጠረዡ አጋማሽ ላይ የሚገኙ ክለቦች ናቸው።

በአቋም ደረጃ መጥፎ ባይሆንም ውጤት ግን ርቋቸዋል።

ኤቨርተን ግቦችን እያስተናገደ በመቆየቱ ይህንን ለማረም እንደሚሞክር አስባለሁ።

ግምት፡ 1 - 0

ሊድስ ዩናይትድ ከ ብራይተን

ይህንን ጨዋታ ለመገመት በጣም ከባድ ነው።

ብራይተን ይህን ጨዋታ አሸንፎ እስከ ስድስተኛ ያለውን ደረጀ ይዞ ማጠናቀቅ የሚችልበት ዕድል አለ።

ሊድስ በበኩሉ ከስፐርስ ጋር ጥሩ ቢጫወት ማሸነፍ ሳይችል ቀርቷል።

ግምት፡ 1 - 1

ዎልቭስ ከ ፉልሃም

ፉልሃም በመጀመሪያው ዙር በቀላሉ ነበር ዎልቭስን ያሸነፈው።

ፉልሃም ከዚህ ጨዋታም ሦስት ነጥቦችን ማሳካት ይችላል።

ግምት፡ 1 - 2

ኒውካስል ከ ዌስት ሃም

ባለፈው ሳምንት የአርሰናሉ ግብ ጠባቂ ዴቪድ ራያ ላይ ጥፋት በመፈጸሙ ዌስት ሃም መሸነፉ ተገቢ ውሳኔ ነው።

ይህ ጨዋታ ግን የግድ ሊያሸንፉት የሚገባቸው ነው።

ኒውካስል በመጀመሪያው ዙር ከመሸነፉም በላይ ዘንድሮው አቋሙ ወርዷል።

ጨዋታው በአቻ ውጤት እንደሚጠናቀቅ እምታለሁ።

ግምት፡ 1 - 1

ሰኞ

አርሰናል ከ በርንሌይ

አርሰናል ከበርንሌይ

የሊጉ ዋንጫ የአርሰናል ነው። ከበርንሌይ ጋር ይህንን የሚያበላሹት አይሆንም።

በቀላሉ የሚያሸንፉት ጨዋታ ይሆናል።

በርንሌይ የተቃራኒ ቡድንን ከማስጨነቅ እልቅ ደጋፊዎቻቸውን ማስጨነቃቸውን ባለፈው ሳምንት ከቪላ ጋር አቻ ሲለያዩ አሳይተዋል።

አርሰናል ከቆመ ኳስም ሆነ በጨዋታ ጎሎችን የሚያስቆጥሩ ተጫዋቾችን ይዟል።

ግምት፡ 3 - 0