የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ ከኦፔክ ነዳጅ አምራች አገራት አባልነት መውጣቷ ምን ተጽዕኖ ይኖረዋል?

ነጭ ልብስ የለበሰ ግለሰብ በበርሜሎች አጠገብ እያለፈ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የንባብ ጊዜ: 4 ደቂቃ

የተባበሩት አብ ኤሜሬትስ (ዩኤኢ) ከፔትሮሊየም ላኪ አገራት ድርጅት (ኦፔክ) እንደምትወጣ በድንገት ማሳወቋ ትልቅ ክስተት ነው።

ዩኤኢ የኦፔክ አራተኛዋ ግዙፍ ነዳጅ አምራች አገር ናት። የሚቀድሟት ሳዑዲ አረቢያ፣ ኢራቅ እና አሁን ከአሜሪካ ጋር ጦርነት ውስጥ ያለችው ኢራን ናቸው።

ኤሜሬቶች እአአ በ1971 አንድ አገር ከመሆናቸው በፊትም አባል ነበሩ። ኦፔክ በዋናነት በባሕረ ሰላጤው የነዳጅ ላኪ አገራት ድርጅት ነው።

ኦፔክ በዋናነት የባህረ ሰላጤ ነዳጅ ዘይት ላኪዎች ድርጅት ሲሆን ለብዙ አስርት ዓመታት ምርትን በመቀነስ ወይም በመጨመር እና ለአባል አገራት ድርሻዎችን በመመደብ የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋን የሚቆጣጠር ድርጅት ነው።

በ1970ዎቹ የነዳጅ ዘይት ቀውሶች ውስጥም ወሳኝ ሚና ተጫውቷል፤ ይህ ደግሞ በሌላው ዓለም የኤነርጂ ፖሊሲን ቀይሯል።

የኦፔክ ምርት በሳዑዲ አረቢያ ቁጥጥር ስር ቢሆንም፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ሁለተኛው ከፍተኛ የመጠባበቂያ ምርት አቅም ነበራት። በሌላ አነጋገር ምርትን በመጨመር ዋጋን ለመቀነስ የሚያስችል ሁለተኛዋ በጣም አስፈላጊ አምራች ነበረች።

በእርግጥም ይህ በትክክል የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አቋምን ለረዥም ጊዜ እንደገና እንድታጤነው ምክንያት ሆኗል። በቀላል አነጋገር የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መዋዕለ ንዋይ ያፈሰሰችበትን ከፍተኛ አቅም ለመጠቀም ትፈልጋለች።

ነዳጅ ማምረቻ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ኦፔክ አባል አገራቱ ምን ያህል ነዳጅ ማምረት እንደሚችሉ ይወስናል። በዚህ ገደብ የተነሳ ዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ በቀን ከ3 እስከ 3.5 ሚሊዮን በርሜሎች ብቻ እንድታመርት አድርጓታል። ይህም ማለት ከሌሎች አባል አገራት ጋር ሲነጻጸር ወሳኝ የሆነ ገቢ በማጣት ረገድ መስዋዕትነት እንድትከፍል ሆኗል።

ይሁን እንጂ የአሁኑ እርምጃዋ የኢራን ጦርነት ያስከተለው መዘዝን ያመለክታል። በባህረ ሰላጤው ውስጥ የተከሰተው ጫና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከኢራን ጋር ያላትን ግንኙነት ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል፣።

ከሳዑዲ አረቢያ ጋር ያላትን የሻከረ ግንኙነትም ሊጎዳው ይችላል።

ለኦፔክ ከፍተኛ ኪሳራ ነው፤ የዩኤኢ ውሳኔ የተሰማው ድርጅቱ አንድነቱን ጠብቆ ስለመቆየቱ እና ለረዥም ጊዜ ውጤታማ ሆኖ መዝለቁ ላይ ጥያቄ እየተነሳ በነበረበት ወቅት ነው።

ዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ የነዳጅ ምርቷን በቀን ወደ 5 ሚሊዮን በርሜሎች እንድታሳድግ ይጠበቅ ነበር። ይህ ሊሆን የሚችለው ግን ዳግም ነዳጇን በባሕርም ሆነ በተዘረጋው የማስተላለፊያ መስመር ለውጭ ገበያ ማቅረብ ስትችል ብቻ ነው።

ሳዑዲ አረቢያ የነዳጅ ዋጋን ለመቀነስ ብዙ በማምረት የዋጋ ጦርነት ልትከፍት ትችላለች። ነገር ግን ዩኤኢ ዘርፈ ብዙ የሆነ ኢኮኖሚ ስላላት ትቋቋመዋለች። ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የኦፔክ አባል አገራት ገቢያቸው በነዳጅ ላይ ብቻ የተመሰረተ በመሆኑ በዚህ ሊቸገሩ ይችላል።

ብዙው ነገር የሚወሰነው በሳዑዲ አረቢያ ምላሽ ላይ ነው።

በዱባይ የባሕር ዳርቻ ላይ የሚታይ የንግድ መርከብ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

Skip podcast promotion and continue reading
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናል

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት

ይህንን በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

End of podcast promotion

ዋና ዋና የኤሚሬቶች ባለሥልጣናት አቡ ዳቢ ከሚገኘው የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የነዳጅ ማውጫዎች የሚነሱ አዳዲስ የማስተላለፊያ መስመሮች አደገኛ የሆነውን የሆርሙዝ ባሕረ ወሽመጥን በመተው ብዙም ጥቅም ላይ ወዳልዋለው ፉጃይራ ወደብ እንደሚያመሩ ይናገራሉ።

በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ደረጃ ጥቅም ላይ እየዋለ ያለው አንድ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ነው። ነገር ግን እየጨመረ የሚመጣውን የምርት መጠን እና በባህረ ሰላጤው ውስጥ የነዳጅ ማመላለሻ ፍሰት እና ዋጋ ላይ ዘላቂ ለውጥ ለማምጣት ተጨማሪ አቅም ያስፈልጋል።

ለጊዜው የሆርሙዝ ወሽመጥን አሜሪካ እና ኢራን በመዝጋታቸው የነዳጅ፣ ጋዝ፣ ፔትሮል፣ ፕላስቲክ እና የምግብ ዋጋ በመናሩ ይህ አንገብጋቢው ጉዳይ አይደለም።

አሁን ዋጋው ጣራ የነካው የነዳጅ ዋጋ በበርሜል 110 እየተሸጠ ቢሆንም ይህ ግን ለረዥም ጊዜ የሚቆይ አይደለም። በወሽመጡ ላይ የተጣለው ገደብ የሚነሳ ከሆነ የነዳጅ ዋጋ በሚቀጥለው ዓመት 50 ዶላር ይደርሳል። ይህ ግን ውጥረቶች የሚረግቡ ከሆነ እና እንደ የአሜሪካ ምርጫ ውጤት ያሉ የፖለቲካ ክስተቶች የሚበይኑት ነው።

ኦፔክ ለዓለም የነዳጅ ገበያ ያለው ጥቅም እንደ1970ዎቹ አይደለም። በወቅቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚገበያየው የነዳጅ ዘይት 85 በመቶ ድርሻ የነበረው ቢሆንም ዛሬ ግን ከ50 በመቶ ብቻ ነው። የነዳጅ ዘይትም ለዓለም ምጣኔ ኃብት ከ1970ዎቹ ያነሰ ወሳኝ ሚና አለው። ኦፔክ አሁን የተወሰነ አቅም ቢኖረውም ጠቅልሎ ግን የዓለም የነዳጅ ዋጋን መቆጣጠር አይችልም።

የኦፔክ መሪ የነበሩት የቀድሞው የሳዑዲ የነዳጅ ሚኒስትር ሼክ ያማኒ "ዓለም ድንጋይ ስለጨረሰች የድንጋይ ዘመን አብቅቷል ማለት አይደለም፤ ዓለም የነዳጅ ሃብቷን ስለጨረሰች የነዳጅ ዘመን ያበቃል ማለት አይደለም" ብለው ነበር።

ይህ የሚያመለክተው ሃይድሮካርቦኖች በሌሎች የኤነርጂ ምንጮች የሚተኩበትን ዓለም ነው።

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እርምጃን ለመረዳት አንዱ መንገድ ዓለም ነዳጅ ላይ ያላት ጥገኛነት እየቀነሰ መምጣቱን የሚያሳይ መሆኑን ነው።

ሌላው ደግሞ የቻይና በኤሌክትሪክ ኃይል ላይ ያላት ኢንቨስትመንት በነዳጅ እና በጋዝ ዋጋ መጨመር ምክንያት የሚመጣውን የኢኮኖሚ ውድቀት ለማስታገስ ረድቷል።

በአንዳንድ ስሌቶች መሠረት ቻይና የምታመርታቸው የቤት ውስጥ እና የጭነት መኪኖች እንዲሁም ባቡሮች ወደ ኤሌትሪክ መቀየራቸው በዓለም ሁለተኛው ትልቁ ኢኮኖሚ ባላት አገር ውስጥ የነዳጅ ፍላጎትን በቀን በ1 ሚሊዮን በርሜል ቀንሷል። ይህ አዝማሚያ በዓለም ዙሪያ እየተፋጠነ ሲሄድ የዓለም የነዳጅ ፍላጎት ሊወርድ ይችላል።

በዚህ መሠረት በተቻለ ፍጥነት ከነዳጅ ክምችት ብዙ ገንዘብ መሰብሰብ ብልህነት ነው።

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በቱሪዝም እና ፋይናንስ ላይ የተሰባጠረ ጠንካራ ኢኮኖሚ አላት። ይህ ግን በብዛት የሚወሰነው በባህረ ሰላጤው ውስጥ ያለው አለመረጋጋት ሲቆም የሚፈጠረው አዲስ የኢኮኖሚ አማራጭ ምን ይሆናል በሚለው ላይ ነው።

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ኦፔክን ለቅቃ መውጣቷ ሌሎች ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስዱ ሊያነሳሳ ይችላል። ይህም በሳዑዲ አረቢያ ላይ ከፍተኛ ጫና ሊፈጥር ይችላል።

የነዳጅ ጫኝ መርከቦች በወሽመጡ ላይ ያለ ስጋት መቅዘፍ ሲችሉ ወይም የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አዳዲስ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመሮችን ለመገንባት የምታደርገውን ጥረት ዳግም ስታጠናክር፣ የኤሚሬትስ ነዳጅ በኦፔክ ሳይገደብ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ መልኩ ለገበያ ይቀርባል።

በአሁኑ ጊዜ በወሽመጡ ላይ በተጣለው ገደብ የተነሳ ብዙም ተጽእኖ አይኖረውም። በኋላ ላይ ግን ሁሉንም ነገር ሊለውጥ ይችላል።