ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
በካሜሩን እየተካሄደ ያለው የ2021 የአፍሪካ ዋንጫ የግጥሚያ ፕሮግራምና ውጤቶች
በኮሮናቫይረስ ምክንያት ለአንድ ዓመት የተራዘመው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከእሑድ ጥር 01/2014 ዓ.ም ጀምሮ ካሜሩን ውስጥ እየተካሄደ ነው።
እተካሄደ ያለውን የአፍሪካ ዋንጫ የግጥሚያ ፕሮግራሞችንና ውጤቶችን ቀጥሎ ከተቀመጠው ዝርዝር ላይ ይመልከቱ።
የውድድሩ አዘጋጅ ካሜሩን በአፍሪካ ዋንጫ በመሳተፍ ከምድቡ ሃገራት የሚያክላት የለም።
ቡርኪና ፋሶ ለ12ኛ ጊዜ፤ ኢትዮጵያ ደግሞ በአንድ ዝቅ ብላ ለ11ኛ ጊዜ ትሳተፋለች። ለውድድሩ እንግዳ ያልሆነችው ኬፕ ቨርዴ የዘንድሮ ተሳትፎዋ ለሶስተኛ ጊዜ ነው።
ከኢትዮጵያ በቀር ሁሉም የምድቡ ሃገራት በአውሮፓ ሊጎች የሚጫወቱ ተጫዋቾቻቸውን ይዘው ነው ወደ ካሜሩን ያቀኑት።
ነገር ግን ከሽመልስ በቀለና ሙጂብ ቃሲም በቀር ሁሉንም ተጫዋቾቿን ከሃገር ውስጥ ክለቦች የመረጠችው ኢትዮጵያ የውድድሩ ክስተት ልትሆን እንደምትችል ብዙዎች ይገምታሉ።