''ምንም አንኳን ኦሮሚያ ለፎቶግራፍ ምቹ ብትሆንም በፎቶግራፍ ትዕይንት ወደ ኋላ ቀርተናል''

ታትሟል

የኦሮሚያን ገጸ-ምድር፣ የጎብኝት መዳረሻዎች እና የኦሮሚያን ባህል ያሚያሳየው የፎቶግራፍ ትዕይንት በአዲስ አበባ የኦሮሞ ማዕከል ለእይታ ቀርቧል።

የቦረና ወጣት ሴት
የምስሉ መግለጫ, የቦረና ሴቶች በቅቤና በተለያዩ የውበት መጠበቂያዎች እራሳቸውን ያስውባሉ። ይሀ ፎቶግራፍ የተነሳው በቦረና ዞን አሬሮ ከተማ አቅራቢያ ነው።
ወጣት ልጅ በጤፍ አጨዳ ላይ
የምስሉ መግለጫ, በአዲስ አበባ ዙሪያ ካሉ አርሶ አደሮች መካከል ይህ ወጣት ያጨደውን ስንዴ ሲያስር።
እናቶች ሲያዜሙ
የምስሉ መግለጫ, ክረምቱ ካለፈ በኋላ ከኦሮሚያ የተለያዩ አቅጣጫዎች በመሰባሰብ ለፈጣሪያቸው 'ዋቃ' ምስጋናን ያደርሳሉ። እነዚህ እናቶች ከአርሲ ዞን ወደ ቢሾፍቱ የኢሬቻ በዓል ለማክበር የመጡ ናቸው።
የኦሮሞ ልጅ በጎጆ ውስጥ
የምስሉ መግለጫ, ይህ ፎቶ የገጠሪቷን ኦሮሚያ ህይወት በከፊል የሚያሳይ ነው። ቦታው ሊበን ጉጂ ዞን ውስጥ ነው።
አጋዘን ወይም ፍየል የሚመስለው ዛፍ።
የምስሉ መግለጫ, ለቦረና ኦሮሞ ፍየሎች ከፍተኛ ቦታ አላቸው። ፍየሎች በአነስተኛ ውሃና የግጦሽ ሣር ድርቅን መቋቋም ይችላሉ። አጋዘን ወይም ፍየል የሚመስለው ዛፍ የተነሳው ያቤሎ ቦረና ነው።
ከረዩዎች ግመሎቻቸውን በመያዝ ሲጓዙ
የምስሉ መግለጫ, እንደሌሎቹ የኦሮሞ ጎሳዎች ከረዩዎች የራሳቸው የሆነ ቦኩ የተባለ የገዳ ሥርዓታ አላቸው። የመጨረሻው የቦኩ የሥልጣን ርክክብ የተካሄደው በ2009 ዓ.ም. ታሬ ሉጎ በምትባል መተሃራ አካባቢ በምትገኝ ቦታ ነው።
የአባ ጅፋር ቤተ-መንግሥት
የምስሉ መግለጫ, ንጉስ አባ ጅፋር ከ1878 – 1932 ጅማና አከባቢዋን አስተዳድረዋል። ይህ ቤተ-መንግሥታቸውም በጅማ ከተማ ኦልከዓ በሚባል አከባቢ ይገኛል።
ፍየሎች ኩይሳ ላይ
የምስሉ መግለጫ, የምስጥ ኩይሳዎች በረሃማ በሆኑ እንደ ቦረና ባሉ አካባቢዎች ላይ ማየት የተለመደ ነው።