
የፎቶው ባለመብት, AP
ሁቲዎች ዓለም አቀፍ እውቅና ያለው የየመን መንግሥት መቀመጫ በሆነው እና በኤደን
በሚገኘው ቤተ መንግሥት ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ተናገሩ።
የሁቲ ታጣቂዎች በኤደን በሚገኘው ፕሬዚዳንታዊ ቤተ መንግሥት ላይ በፈጸሙት የሚሳዔል ጥቃት አምስት ሰዎች መገደላቸውን
እና 16 መቁሰላቸው ተገልጿል።
የአገሪቱ ማስታወቂያ ሚኒስትር ሞአማር አል ኢራይኒ ለቢቢሲ አምስት ሚሳዔል መተኮሱን ገልጸው የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር
እና ሌሎች ሚኒስትሮች ምንም ጉዳት አልደረሰባቸውም ብለዋል።
በየመን ወደብ ከተማ ኤደን የሚገኘው እና የመንግሥት መቀመጫ የሆነው ቤተ መንግሥት አቅራቢያ ሐሙስ ዕለት ቢያንስ ስድስት ፍንዳታዎች መከሰታቸውን የዐይን እማኞች ተናግረዋል።
በኢራን በሚደገፉት የሁቲ አማፂያን እና በሳዑዲ አረቢያ በሚመራው ጥምረት መካከል የሚካሄደው ግጭት እየተባባሰ ከመጣ ወዲህ በቤተ መንግሥቱ አካባቢ የተፈጸመው ይህ ጥቃት ያልተለመደ ክስተት ነበር።
ፍንዳታዎቹ በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤ የፈጠሩ ሲሆን አካባቢውን ለቅቀው እንዲሸሹም አድርጓል።
የየመን ጤና ሚኒስትር ቃሲም ቡሃይቤህ በበኩላቸው ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል የቤተመንግሥቱ ጥበቃዎች እና ሌሎች ሠራተኞች እንደሚገኙበት ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ሻያ ዚንዳኑ “ጭካኔ የተሞላበት” ያሉትን ጥቃት አውግዘው ሁቲዎች “የወንጀል ባህሪያቸውን ቀጥለውበታል’ ብለዋል።
በኤደን ከተማ የሚገኘው የሳባ የዜና ወኪል በበኩሉ መንግሥት ሁቲዎች በሚሳዔሎች እና በድሮኖች ጥቃት መፈጸማቸውን መናገሩን ዘግቧል።
አንድ የጸጥታ ባለሥልጣን እንደገለጹት፣ ቢያንስ ሁለት ፍንዳታዎች በማሺቅ ቤተ መንግሥት አቅራቢያ በሚገኘው ኮረብታ ላይ የተከሰቱ ሲሆን፣ ሌሎች ሁለት ፍንዳታዎች ደግሞ የጸጥታ አካላት መግቢያ በር አካባቢ ተፈጽመዋል።
አብዛኛዎቹ የየመን መንግሥት ኃላፊዎች በስደት ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ በኤደን ከተማ ያሉት ደግሞ ደህንነታቸው የተጠበቀ መሆኑን አንድ የመንግሥት ባለሥልጣን ተናግረዋል።
በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እየተሰራጨ የሚገኝ እና አሶሼትድ ፕሬስ ትክክለኛነቱን ያረጋገጠው አንድ ቪዲዮ ቤተ መንግሥቱ በሚገኝበት አካባቢ ጭስ ሲወጣ ያሳያል።
ሁቲዎች የሳዑዲ ጦር ዘመቻ ዋና መምሪያ ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን አስታውቀዋል።
ይህ የአማፂያኑ እርምጃ በሳዑዲ አረቢያ ግዛት ውስጥ በሚገኙ አውሮፕላን ማረፊያዎችና የነዳጅ መሠረተ ልማቶች ላይ የፈጸሙት ተከታታይ ጥቃቶች አካል መሆኑን አስታውቀዋል።
ከዓለማችን ዋና ዋና የነዳጅ ላኪ አገራት አንዷ የሆነችው ሳዑዲ አረቢያ ተደጋጋሚ ጥቃቶች እየደረሱባት በመሆኑ የኢራንን ጦርነት ለማስቆም የሚደረጉ ጥረቶችን አወሳስቦታል።
አማፂያኑ አየር መንገዶች የሳዑዲ አረቢያን የአየር ክልል እንዳይጠቀሙ ማስጠንቀቂያ በመስጠታቸው፣ በክልሉ የሚደረጉ የአየር ጉዞዎችም ተስተጓጉለዋል።
ፍላይት ራዳር 24 ወደ ጂዳ አውሮፕላን ማረፊያ የሚደረጉ በርካታ በረራዎች መሰረዛቸውን
አስታውቋል።